Komentar baru

Advertisement

ቁርጥራጭ ሃሳቦች ፪

Eriyot Alemu
Oct 10, 2024
Last Updated 2024-10-17T12:23:00Z
Advertisement

 


በአዳም ረታ ግራጫ ቃጭሎች ላይ የሆነ ሰው የሆነ ሀሳብ ሰነዘረ። አንድ ወዳጄ ደግሞ ምን ትላለህ ብሎ ስሜን ሸነቆረው በሌለሁበት… እዚሁ ሰፈሬ ሆኜ የሆነ ነገር ልበል፡፡ ቀጥታ ከምመልስ እንዲህ ላርገው፡፡


የትኛውም መፅሃፍ በተጀመረበት መንፈስ አይቀጥልም፡፡ ወይ ከፍ ወይ ዝቅ ይላል፡፡ ይህ አዙረን ካየነው የደራሲውን ሰውኛ ባህሪ የሚያሳይም ነው፡፡ ሰው ለዘላቂ ጊዜ ወጥ ባህሪ አይኖረውም፡፡ አሁን የማወራው ስለ ልብወለድ ስለሆነ…. አንድ ደራሲ አንድን ልብወለድ ጀምሮ ለመጨረስ በትንሹ ወራትን ይፈጅበታል፡፡ በነዚህ ወራት ውስጥ ደግሞ ቋሚ ባህሪ (ሙድ) አይኖረውም፡፡ እናም በዚህ የደራሲው የሙድ መቀያየር ውስጥ ስራውም መልኩን ይቀያይራል፡፡


የአንድ ልብወለድ ሲጀመር እስኪጨረስ ያለው የመልክ መቀያየር በብዛት ልብ የማይባለው ኮስተር ባሉ ስራዎች ላይ ይመስለኛል፡፡ ያው አንባቢ ሳያውቀው ልዩነቱን ሊረዳ ቢችልም… እንደ ቀልድ አዘል ስራዎች ግን የተጋነነ አይሆንም፡፡


ዘውጋቸው በቀልድ የተለወሰ ስራዎች ግን ልዩነታቸው አፍጥጦ ይወጣል፡፡ ደራሲው በጀመረው የሳቅ (የቀልድ) መንፈስ እስከመጨረሻው መቀጠል እጅግ ከባድ ይሆንበታል— ብዙውን ጊዜ፡፡


በግሌ ስጀምራቸው ሳቅ የጫሩብኝ፣ ቁምነገር አዘልም 5 ረዥም ልብወለዶችን ላንሳ


፩) Botchan በnatsume soseki


የጃፓኖች ተወዳጅ መፅሃፍ ነው፡፡ እስከ መፅሃፉ አጋማሽ ድረስ ሲጀመር የነበረው የቀልድ ከፍታ የለም፡፡ ኮሚካዊ አፃፃፉ ማለቴ ነው፡፡


፪) Children of the Revolution በDinaw Mengestu


ሲጀመር በሳቅ ይጀምርና ጠፋ ብሎ...እንደገና ሳቅ... እንደገና መጥፋት ነው፡፡ ገፀባህሪያቱም ለሳቅ ምቹ ናቸው፡፡ እንደ ዲናው ሌሎች ስራዎች ስደት ላይ ኮስተር ብሎ ሲያተኩር ሳቁ ይዋጣል፡፡


፫) A modern marriage በDinah Kealy


1988 የታተመ መፅሃፍ ነው፡፡ በተመሳሳይ ርዕስ ብዙ መፅሃፍም አለ፡፡ ይህ መፅሃፍ ከግማሽ በላይ የቀልድ ይዘቱን ይዞልኝ ቀጥሏል፡፡ መፅሃፉ በቀልድ የተዋዛ እጅግ ቁምነገራም ነው፡፡ በግል ስለ ትዳር ሳስብ ሳስብ ሁላ አስበዋለሁ፡፡ ቤቴ እንዲኖረኝ ተመኝቼ ፈልጌ ፈልጌ ያጣሁት መፅሃፍ ነው፡፡ መጥሃፍ ስጦታ የምሰጡ ሰዎች አስቡበት ሃሃሃ



፬) Standard Deviation በkatherine heiny


ከርዕሱ ጀምሮ “መፅሃፍ እንዲህ ብቻ ነው የሚፃፈው ማነው ያለው?" ብሎ በነገር የሚጀምር መፅሃፍ ይመስላል፡፡ ምናልባት ከ75% በላይ የቀልድ ይዘቱን ያለቀቀ መፅሃፍ ነው፡፡ ደራሲዋ single, carefree, mellow በሚለው ሌላ ስራዋ እንዳረጋገጥኩት ለቀልድ የተሰጠች ነች፡፡


ብዙ ጊዜ መፅሃፍ ጀርባ ላይ የሚፃፉ አስተያየቶች ሽንገላ ቅብ ናቸው ብዬ ስለማስብ አዕምሮዬ ላይ የቀረ ብዙም አስተያየት የለም፡፡ እዚህ መፅሃፍ ላይ ያለ አንድ አስተያየት ሰጪ “ምናለ ደራሲዋ ጓደኛዬ በሆነች" ነው ያለው፡፡ መፅሃፉን ገላጭ ይመስለኛል፡፡


፭) ግራጫ ቃጭሎች በአዳም ረታ 


በአማርኛ ልብወለድ ታሪክ ዕንባዬ እስኪወርድ ያሳቀኝ መዝገቡ ዱባለ የተባለ ገፀባህሪ ነው፡፡ ከአዳም ስራዎችም ብዛት ሳቅ ያለው መፅሃፍም ይሄ ነው፡፡ ግን ግራጫ ቃጭሎችም በተጀመረበት መንፈስ አላለቀም፡፡ በርግጥ ከሆነ ገፅ በኋላ (አሁን መፅሃፉ እጄ ላይ ስለሌለ) ምናልባት ከክፍል 2 በኋላ በጣም ፍዝነት አለው፡፡ ሁለት የተለያየ ሰው የፃፈው እስኪመስል ድረስ፡፡ ሆኖም ስሜቱን የፈጠረው ከላይ መግቢያዬ ላይ ያነሳሁት ሃሳብ ይመስለኛል። 


ሳጠቃልል፦ አንዳንድ አድናቂዎች መታረም ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ አንድን ሰው ስታደንቅ ምንም ጎዶሎ ስሜት አይሰማህም ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ እኔ አዳምን እጅግ ከልቤ ባከብረውም ባደንቀውም ዘወትር ብደመምበትም በስራው ያየሁትን ክፍተቶች ግን ሁሌ እጠቁማለሁ፡፡ አንዳንዶች ግን ስታደንቁ ጨፍናችሁ አይሁን ሃሃሃ


መከራከሪያችሁም እንዴት እከሌ ስለ አዳም ይፅፋል ሳይሆን እከሌ ስለ አዳም ምን ፃፈ? የፃፈውስ ውሃ ያነሳል ወይ? ወዘተርፈ ነው::


በርግጥ አስተያየት ሰጪው ነጥቦች ቢኖሩትም አስተያየት የሰጠበት መንገድ ግን የጋጠወጥ ነው፡፡ ግልባጭ ለቤተሰቦቹ መልሰው ቆንጥጠው እንዲያሳድጉት ይሁን ሃሃሃሃ


iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

8 comments:

  1. ጋሽ እንደ ልቡ ምኞቴ አንድ ወር እንኳ እንዳንተ በነፃነት ኖሬ መሞት ነው። ሱስ ወስጥ ሆነህ በነፃነትህ እቀና ነበር። ሱስ ስትተው በመቻልህ ቀናው። የምታረገው ሁሉ ኑሮህ ያስቀናኛል። የውነቴን ነው ምኞቴ እንዳንተ ቢያንስ አንድ ወር መኖር ነው። ይመችህ ብቻ።

    ReplyDelete
  2. ዛሬ ቀንህም አደል? መፅሃፍ ስጦታ የምሰጡ ላልከው የሳሙኤል ልጅአለም መፅሃፍ ተዘጋጅቶልሃል። በዚ ዳግማዊ ልደቴ በምትለው ቀን ልነግርህ ነው ዝም ያልኩህ። ሃፒ ሃፒ ዳግማዊ ልደት!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሰዪዬ ይግረምሽ ጋሽ አብዱ የሚባሉ ሰው አገኝልሃለው ብለውኝ ስለነበር ትላንት ራሱ እነ ጌቱ ሰፈር ሄጄ ነበር። እኔ መች አውቄ? አንቺን አልጠየኩሽም ነበር። ምክንያቴንም ታውቂያለሽ። የሰው ውለታ መሸከም ቢያስጎነብስ ኖሮ ያንቺ ውለታ እኔን መሬት ይደፋኝ ነበር። አንቺና ማሂን ማመስገን ትክት ብሎኛል። ምን አይነት ሰው ነሽ ግን? ከዛ ደብተራ ጋር ያወራነውን ሰምተሽ መሆን አለበት መፅሃፉን እንደምፈልገው ያወቅሺው።

      ሰዪይ ሰዓት ከቀየርኩ ወዲህ ሰፈራችን እንዴት እንደራቀኝ ታውቂያለሽ። ብዙ ብዙ ነገር ነው የናፈቀኝ። የዛ ጉረኛ ደብተራ ፍላቴው ሁሉ ናፍቆኛል ሃሃሃሃ በዛውም ግን እስከ ቅዳሜ ከመጣ መፅሃፉን ሰተሺው እዛው ያንብብ ይዞ እንዳይሮጥ ሃሃሃሃሃሃ

      በዛውም ይሄን በይልኝ…..ሳሙኤል ልጅአለም (ስሙ የዚ ዘመን ቢመስልህም ቅሉ፣ ቅልህ ይፍረስና) ሃሃሃሃ 1982 ላይ ወንድ ሆኖ በሴት ፆታ የፃፈ ሰው ነው። አንተ ካልከው ሰው ይቀድማል አትደምድም አንተ ደምዳሚ ሃሃሃሃ ከዚም መፅሃፍ በተጨማሪ 1991 የታተመ ያፈነገጠ ወጥመድ የሚል መፅሃፍ ያለው ራሃ የሆነ ሰው ነው። ብዙ ፅፎ አብሬው ውዬ ፖዘቲቭ ጮራዬን በኮመኮምኩ የምለው ሰው ነው። በጮራዬ እንዳትስቅ አንተ ጮራቅ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

      ሰዪነት እስክመጣ ድረስ ስለቀኑም ስለሁሉም ነገር ግን አላህ የልብሽን መሻት ሁሉ ይፈፅምልሽ። ቡዙ ጊዜ እንዴት አርጌ ላመስግናት እያልኩ በብዙ ስለምጨነቅ፣ ሲያቅተኝ አቦ ትንካው በቃ እላለሁ በሆዴ ሃሃሃሃ ብቻ ዘወትር እንደራሴ ምኞት ነው ሁሌ ዱአ የማረገው…… ሰይ እመኚኝ ይሆናል ደሞ። ኢንሻአላህ!!!!!!!!!!!

      Delete
  3. ይቅርታ ወንድሜ በወሬያችን መሀል ገባህ አትበለኝና የሳሙኤል ልጅዓለም መፅሃፍ ግጥምጥም እና ያፈነገጠው መንደር ነው ወይስ ያፈነገጠ ወጥመድ? እርግጠኛ ለመሆን ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. አብረን ብንበላ ምን ይመስላችኋል ተብሎ አፍጠው በሚቀላቀሉበት በዚ ብርቅዬ ዘመን፣ በወሬያችሁ መሃል ጣልቃ ስለገባው ይቅርታ ታላቅ ትህትና ነው ወንድሜ ሃሃሃ

      ጉዳዩ ሃገራዊ መፅሃፍ ነውና ይመለከትሃል። ወደ ጉዳዩ ስገባ ጥሩ ጎግለር ነህ ብዬ ልጀምር። ያፈነገጠው መንደር የሚለውን ያገኘኧው 1999 (በፈረንጅ) በወጣ እንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ ነው። ሳሙኤልን ኢንተርቪው ያረገችው ሴት መግቢያው ላይ የሰራችው ስህተት ነው። የሆሄ እንኳ መቀራረብ የፈጠረው ስህተት አይደለም። መንደር እና ወጥመድ በጣም የተራራቁ ናቸው። ያፈነገጠው መንደር እንደውም የፍልስፍና መፅሃፍ ርዕስ ይመስላል። ለሌሎች ደራሲያን አሪፍ ጥቆማ ነው ሃሃሃ ያው ስህተት ያለና የሚኖር ነው ብለን እናልፈዋለን።

      የሳሙኤል ትክክለኛ መፅሀፍ ግን ያፈነገጠ ወጥመድ ነው። ወጥመዱን የሚያዘጋጀው አንድ ሰካራም ገፀባህሪይ ነው። የመፅሃፉ የሽፋን ስዕል ሁሉ ሰካራሙ ከነጠርሙሱ ነው። እና በዚህ እርግጠኛ ሁን። አመሰግናለሁ!

      Delete
  4. ኤ ሞደርን ሜሬጅን ወመዘክር አግኝቼ አነበብኩት። አስቂኝም በቁምነገርም የተሞላ ነው መቶ በመቶ እስማማለሁ። አጠቃላይ ለነገሮች ያለህ አረዳድ ግን እጅግ እጅግ የሚገርም ነው። የሚስቅም የሚያስቅም ፈላስፋ አንተን አየሁ። ብዙ እየተማርኩብህ ነው። መመለስ ከፈለክ ብቻ መልስልኝ። ከመፅሃፉ ገፀባህሪያት ከማን ጎን ቆመህ ነበር? ከኢንጂነሩ ወይስ ከደራሲው?

    የገረመኝን ነገር ልንገርህ የእንዳለ ጌታ ከበደ ደርሶ መልስ መፅሃፍ ለንደዚህ አይነት አፃፃፍ መሳ ሆኖ ሳገኘው እንዴት ደስ እንዳለኝ። አዳም ረታ ከቅርፅ ለውጥ ጋር ይሄን አፃፃፍ ይጠቀማል። አሁን በቅርቡ ደግሞ አሌክስ አብርሃም አልተዘዋወረችም መፅሃፉ ላይ ሞክሮታል። አፃፃፉ ጥንቃቄ ማስተዋል እጅግ ማሰብ ይፈልጋል። እዚህ ላይ ቀልድ መጨመርና ያን ለረጅም ጊዜ ማስኬድ ችሎታ ይፈልጋልና ኤ ሞደርን ሜሬጅ ኤ ፕላስ ይገባዋል። ነገሮችን በዚ መልክ ማየት ካንተ ተምሬ ነው።

    እንደ ቀልድ ኢንተርኔት ላይ ያወኩት ልጅ የሚፅፈው እያንዳንዱ ነገር እኔ ጋር ደመና ይሰራል ብዬ አስቤም አላውቅም ነበር። የሆነ አስተያየት ሰጪ እንዳለው ከአድናቂነት ወደ ካዳሚነት ተቀይሪያለሁ። በነገርህ ላይ ብዙ ሰው የማደንቅ ሰው አይደለሁም። እጅ አሰጥተ ኧኝ ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንዴ ይሄንንማ ራሴ ነኝ የፃፍኩት ብዬ ግግም ብልስ ራሴን ባላደንቅም ቅሉ ሃሃሃ እያዩ በተመስገን ፅሁፍ ነው መጀመሪያ የተኮማተርከኝ። (ኮመንት የሰጠኧኝ) ሃሃሃ …

      አድናቆቱ ባይገባኝም እጅግ አመሰግናለሁ በጣም ከልቤ። ምን አስባለሁ መሰለህ ሁሌም ታርጌት የማረገው አንድ የሆነ ጥግ ላይ የተቀመጠ ከኔ የተሻለ፣ እኔ ያላየሁትን የሚያይ አንድ ሰው አለ። ያ ሰው ምን አይነት ነው ብባል መልሴ እኔንጃ ነው። እያዩ ግን እሱ ሰው ነው ማለት እችላለሁ። ከሰጠኧኝ የእስካሁን አስተያየቶችህ ተነስቼ ልገምትህ አልኩና ተውኩት። እንዲሁ ሳላውቅህ መቀጠሉን ፈለኩ።

      ለአስተያየቶችህ በጣም ልዩ ቦታ ነው ያለኝ። ባላውቅህም ሳላውቅ ሳጠፋ ገስጠኝ ስልህ ከልቤ ነው። ግሳፄህን አምነዋለውም ልክም ነው ብዬ ከወዲሁ ወስጃለሁ። እንዲህ የምለው ሰው ጥቂት ነው። ከምስጋናም ከአክብሮትም ጋር።

      ወደ ጥያቄህ ስሄድ ለምን እንደጠየከኝ ገብቶኛል። ለኢንጂነሩም ለደራሲውም ውግንና አላሳየሁም። እንደ ገፀባህሪው ደራሲ ሳይሆን እንደመፅሃፉ ደራሲ ነው ዝምብዬ ያየኋቸው። አሁን ላይ አጠቃላይ ደራሲው ምን ሊል ፈለገ ነው የሚያሳስበኝ። መልህክት። እሱ ስለገባህም ነው የጠየከኝ። መለስኩት ብዬ አስባለሁ። እጅግ እጅግ ልባዊ ምስጋናዬ ይኧው!!!!!

      Delete
  5. ድጋሚ መጣሁ። ዛሬ አዳም ረታ አንድአፍታ ከእንዳለጌታ ከበደ ጋር ያደረገውን ቆይታ እያየሁ ነበር። በመሃል ስለ ስብሐት ፂም ስራው ሲያወራ ልክ አንተ እንዳልከው ነበር በአጭሩ ያለው። እንደውም አንተ ገፋ አርገህ እንደገለፅከው አስታውሳለሁ። የፈጠርክብኝን ተፅህኖ አንተም እንድታየው ለኔም ምክንያቴን አፅንኦት እንድሰጠው ነው የምነግርህ። ፅሁፉን ግን አሁን ስፈልግ አጣሁት። ሰርች አድርጌም ሞከርኩት። ጠፍቶ ይሆን?

    ReplyDelete

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement