Advertisement
"ሲበዛ ጨካኝ ነው! ሲበዛ!"
"ምናረገ በናትሽ?"
"ዶሮዋን እንዴት ዘቅዝቆ እንደያዛት ብታይ?!"
"እውነትሽን ነው ዘቅዝቆ ያዛት?"
"ብነግርህ አታምነኝም!"
ከነዚህ ባል እና ሚስት ጋር ነው ቀጠሮ ያለኝ፡፡ እስኪመጡ ድረስ ቡና አዝዤ እየጠበኳቸው ነው፡፡ ያገኘሁላቸውም የቤት ሰራተኛ አብራኝ አለች፡፡
"ኢቺ ነች?" አለች ሚስትየው ገና ቁጭ እንዳለች
"አዎ ....." ምን ሆነችብሽ ማለት ከብዶኝ ዝም አልኩ
"ትንሽ በጣም ሲበዛ ቀላች"
"ድመት ትወጃለሽ?" ባልየው ቀጠለ፡፡ ሰራተኛዋ ግራ በመጋባት እኔን ታየኛለች
"አይ…ለእንስሳት ያለሽ ፍቅርሽ እንዴት ነው ማለቱ መሰለኝ… ለምሳሌ ድመት ቤት ውስጥ ቢኖር ምን ይሰማሻል እንደማለት ነገር..." አልኩ አማርኛን በአማርኛ ሳስተረጉም፡፡
"ጥቁር አይሁን እንጂ ግድ የለኝም" ሰራተኛዋ ትከሻዋን ሰበቀች
"ሬሲስት ሬሲስት ሬሲስት..." ሚስትየው ቀወጠቺው፡፡ ባልየው ካልመታኋት ብሎ ተጋበዘ፡፡
እንደፈረደብኝ በአንዳንድ አካባቢ ለጥቁር ድመት ያለውን አመለካከት ረዥም አብራራው፡፡ ባልየው ይሄን እጅግ ጎጂ ባህል ሊታገለው ቃል ገባ፡፡ ሚስትየው ተረጋጋች፡፡
"ሳሚ እንኳንም ጥቁር አልሆነ" ባልየው ፈገግ አለ
"ሳሚ የድመቱ ስም ነው?" ጠየኩ
"አዎ ፍቅር የሆነ ድመት ነው፡፡ ያገኘውን ሁሉ ይስማል… ሳሚዬ" ሚስትየው ተኩራራች፡፡
ሚስትየው ቀጠለች...
"ስለ ሳሚ ጥቂት ልንገርሽ… ሳሚዬ ሲቀሰቅሱት አይወድም፡፡ ልብስ አለሽ?" አሁንም ሰራተኛዋ አፍ
የሌላት ይመስል ዞራ አየቺኝ
"ይኧው በፌስታል የያዘችው" አልኩ፡፡
"አይ ወፈር ያለ ሙሉ ኮተን… ቆይ እኔ እገዛልሽና ከደሞዝሽ ላይ ይቆረጣል፡፡ አየሽ ሳሚ ቶሎ ሰው
ስለሚለምድ… ላይሽ ላይ ሲተኛ ሊበርደው፣ላይመቸው ይችላል" .... ባልየው በደስታ
"ሚስቴ እኮ ደግ ነች" አለኝ፡፡ ወደየት አቅጣጫ እንደሆነ ባላውቅም ራሴን በአይዎንታ አነቃነኩ፡፡
"የምግብ ምርጫሽ ምንድነው?" ባልየው ጠየቀ
"ኧረ እኔ ያገኘሁትን ነው የምጨረግደው" አለች፡፡ ትንሽ ድፍረት እየታየባት ነው፡፡ የምጨረግደው ጠንካራ ቃል ነው፡፡
"እኛ ፍሩታሪያን ስለሆንን አንድ ቤት ስለምንኖር አንቺም ፍሩታሪያን መሆን አለብሽ!" ሰራተኛዋ 'ምን ጉድ ነው?' ፊት አሳየቺኝ፡፡ 'ኧረ ለኔም ግራ ነው' ፊት አሳየኋት፡፡
"በግቢያችን ውስጥ ብዙ ፍራፍሬ አለ፡፡ እና ሳሚ ሲተኛልሽ አትክልቶቹን ትንከባከቢያለሽ…. እኛ ደግሞ የተቆረጠ ስለማንበላ በራሳቸው የሚረግፉትን በጥንቃቄ ትለቅሚያለሽ..."
"ሳሚ አይጥ አይበላም?" አለች ሰራተኛዋ ወሬ መቀየሯ ይሁን አልገባኝም፡፡
"ምን በወጣው" እኩል መለሱላት፡፡
"እና ምንድነው የሚበላው?" ብዬ ጥያቄውን ተቀላቀልኩ፡፡
"ወተት እና ሳምባ ነው" ትንሽ ሳምባ የሚለውን ሰምቼ ተረጋግቼ ሳልጨርስ… ባልየው ቀጠለ
"የታረዱ እንስሳትን ሳምባ አይደለም… በተለያየ ምክንያት የሞቱ እንስሳትን ሳምባ ነው… ለምሳሌ በአደጋ"
መኪና ሲያሽከረክር የሞተ በሬ ሳምባ አስቤ ለሳሚ እኔን ደስ አለኝ፡፡
"ስምሽ ማነው?" ሚስትየው ጠየቀች
"ማርሸት" ሰራተኛዋ መለሰች
በቦታው ላይ እኛ የሌለን ይመስል ማር እና እሸት ይበላል አይበላም ተከራከሩ፡፡ ሰራተኛዋ 'ሊበሉኝ ነው እንዴ የሚቀጥሩኝ?' ፈገግታ አሳየቺኝ፡፡ 'ግዴለም አይበሉሽም' ፈገግታ መለስኩላት። ሚስትየው ኮስተር ብላ..…
"ከዛሬ ጀምሮ ብርቱካን ነው የምንልሽ" አለቻት፡፡ ብርቱካንም ግድየለኝም ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ ፈታ ማለት ጀምራለች፡፡
"'ዶሮ ትችያለሽ?' የሚል ጥያቄ ሰልችቶኝ ነበር" ቀጠለች ብርቱካን
"እና ትችያለሽ?" ሁለቱም እኩል ጮሁ፡፡
"ምናረኳቹ? ለዛ አይደል እንዴ ከቤት ቤት የምንከራተተው፡፡ እንዴት እኔ ብርቱካን ዶሮ እችላለሁ? ..." ዞራ ጠቀሰቺኝ፡፡
የብርቱካን ባህሪ እያፈጠጠ እያገጠጠ ሲመጣ ተነስቼ መሄድ እንዳለብኝ ገባኝ፡፡
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሀሀሀሀሀሀሀ ቤዝድ ኦን ትሩ ስቶሪ ይልሀል ጃ ሃሃሃሃ ሃና ደውላ ነግራኝ እኮ ነው ሳሚ ሲቀሰቅሱት አይወድም ትን ብሎኝ ነበር ሃሃሃ አንድ ደራሲ ያያትን የካርቶን ቤት የውነት መኖሪያ ቤት አሳክሎ ያሳይሀል አለ ታላቁ ደራሲ ግዛቸው አይምሬ ሃሃሃሃሃሃሃሃ ሃይ በልልኝ ግዜን ሃሃሃሃ
ReplyDeleteሃሃሃሃሃሃሃሃ ዘመን አይሽሬው ስመጥሩ ሩቅ አላሚው ግዜማ ምን ያላለው አለ? አንዴ በላቸው ሾው ላይ ቀርቦ “ዉሃው ውስጥ ዘለህ ስትገባ ከደቂቃ በኋላ ውሃው ቡልቅ ቡልቅ ካለ አንተ ጥሩ ልብ አለህ ማለት ነው” ያለው መቼም አይረሳኝም። እንዴት ነው ነገር የሚከሰትለት ግን ሃሃሃሃሃሃ
Deleteሃኒን ደግሞ የብስራት ሱራፌልን እረፊ እረፊ እረፊን እያዳመጥኩ ነው በላት… “እረፊ እረፊ እረፊ አንድ ነገር ብሆን ካንቺ ራስ አልወርድም” ሃሃሃሃሃሃሃሃ