Komentar baru

Advertisement

ለአንዳንድ ኢአማንያን…

Eriyot Alemu
Jun 27, 2022
Last Updated 2023-01-29T13:50:52Z
Advertisement
ምክንያታዊ ኢአማኒ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሁሉ ቢያነበው ባይጠቅመው አይጎዳውም ብዬ አስባለሁ። ምንም ዓይነት ድምዳሜ የሌለው ክፍት የሆነ ብሎግ ስለሆነ፣ ሃሳብ ለሚዘውረው ሰው ባያተርፍ አይጎድልበትም ብዬ ልቀጥል። 

 (ጤናማ ኢኣማኒነት፣ ሰው ተፈጥሮን (ስነ ፍጥረትን) የሚያስስበት አንደኛው መንገድ እና ሰፊ ልብ ያለው ሰው ዘው ብሎ የሚገባበት ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ። አምኜም እቀጥላለሁ!) 
 (ኢጤናማ ኢኣማኝነት እንደሚታየው ኢ-ኢ ይበዛዋል) የሌሎች ሁሉ ስህተት ነው ብሎ ደምድሞ ስለጀመረ፣ ጥረቱ ሁሉ ያንን ፕሩቭ ፍለጋ ነው። ብዙ ጊዜም አቋቋሙ፣ ከተማሳሳይ ሃሳብ ካላቸው ጋር ብቻ ሲሆን ታዝበናል። ለአዲስም ሀሳብ ዝግ ነው) አንዳንዶቻቹ ግን እንደዛ አይደላቹምና የሚከተለውን ልላችሁ ወደድኩ (ቴዎፍሎሶች ሆይ ብዬ ልጀምርልህ እንዴ? :-D ) 

 ከኔ በተቃራኒ የቆመ ሃሳብ ሳገኝ ነው፤ እኔ በራሴ የቆምኩበት ሃሳብ እንዳለኝ የሚሰማኝ። ስለዚህ የተለየ ሃሳብ ጥግ ድረስ አድናቂም ወዳጅም ነኝ፤ በምንም ጉዳይ ላይ። እና የኢኣማንያን ጥያቄዎች ያብቡ፣ ይለምልሙ፣ ይብዙ ባይ ነኝ። ሆኖም አንድ ጤናማ ኢኣማኝ ጥያቄው (የቢሊየን አመታት እንደመሆኑ መጠን) መልሱን ሁሉ ከአንድ ወቅት፣ ከአንድ ሰው (ተቋም)፣ ከአንድ አይነት መስመር ብቻ (ለምሳሌ ንባብና ማሰብ) ከጠበቀ ምኑን ኢኣማኒ ሆነ? ምኑን ሰፊ ልብ ኖረው? ወደ ጉዳዬ እየተንደረደርኩ ነው… 

ዛሬ የማነሳው ሃሳብ፣ የማንንም ጥያቄ ለመመለስ አይደለም። ሰዎች በተለየ ሁኔታ ካዩት ነገር ይልቅ፣ እንዲህም ቢያዩት የሚለውን ስሜት ለማንፀባረቅ ነው። ሰው ካየው ነገር ይልቅ በሚያይበት መንገድ መሄድ አንዳንዴ ጥሩ ነው። ጥሩ ነው ብለንም እንቀጥል። ጀመርኩኝ… 

በአመዛኙ ሁለት አይነት ኢአማንያን አሉ ብዬ አስባለሁ። 
=> አንደኛዎቹ ሃይማኖቱን በጥልቀት ያውቁትና ሳይንሱ ላይ ፈዘዝ ያሉ ሲሆኑ 
=> አንደኛዎቹ ደሞ ሳይንሱ ላይ እሳት ሆነው ሃይማኖቱ ላይ ኔፕ የሆኑ ናቸው። 
(ሁለቱም ላይ ፈዘዝ ያሉና ሁለቱም ላይ እሳት የሆኑ የዛሬ አጀንዳዎቼ አይደሉም) እኛ ሀገር በብዛት ያለው የቱ እንደሆነ፣ ጥያቄ ጭሬ ልለፈው። አንድ ነገር ግን ልበል… ሰዎች ፈርተው ብቻ ሃይማኖተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግልፅ እንደሆነ ሁሉ… አንድ ኢአማኒም ሳይንሱን በመፍራት ብቻ ኢአማኒ ሊሆን ይችላል። በልቡ ሳይንስ አይመረመርም ብሎ አምኗልና!!! ሳይንስን ሳይንስ ከሚያስበው ውጪ የምንጊዜም ልክ አርጎ ተቀብሏልና!… ስለዚህ ፍርሃት አይነቱ ይለያይ እንጂ እዚም እዛም ፈርቶ ማመን አለ ማለት ነው። 

 ነጥቤ ምንድነው? ሃይማኖቱም ውስጥ ሳይንሱም ውስጥ በጥልቀት የሚዋኙ ሰዎች በብዛት እስኪኖሩ፣ ኖረውም እስኪያወሩ ድረስ… አንዱን ካንዱ ይጋጫሉ ብሎ መደምደም ፍፁም ተገቢ አይመስለኝም። ሁለቱም እጅግ ሰፊ ናቸውና! 
* ሃይማኖቱ ያለቀ (የመጨረሻው እውነት ሲሆን) በአማኙ ዘንድ… 
* ሳይንሱ ደሞ ራሱን ከዛሬ ነገ እያሻሻለ የሚመጣ ሂደት ነው፤ በአግባቡ ተረድቶ በተቀበለውም ዘንድ… (ሳይንስ ትላንት አሮጌ ያለውን ዘመናዊ ብሎ ሊያድስ ሙሉ ስልጣን አለው!… ትላንት ልክ ያለውን ዛሬ ስህተትም ሲል ነበር፣ ወደፊትም ይላል) (ሳይንስ በየዘመኑ የሚነሱ ድምር ሰዎች ውጤት ነውና… ያለቀ ነገር ሊኖረው ቢችልም፣ ፍፁም ያለቀ ግን ሊሆን አይችልም) የዛሬው አጀንዳዬ (ይሄን ጉዳይ በዚስ በኩል ብታዩትስ?) የሚለው ሃሳብ መሰንዘር ነውና እንቀጠል… 

ከSteady state universe theory በኋላ evolutionary universe theory መጣ። አሁንም ጉዳዩ ያለቀ አይደለም። ስለ ሁለቱ ልዩነት ጎግል የማያረግ ምኑን ኢአማኒ ሆነ? ምኑን ተመራመረው? :-) :-) እዚጋ ሊቁ አንስታይን በsteady state universe theory መጀመሪያ የነበረው አቋምና ወደ በኋላ የነበረው አቋም ልዩነትን ማየት ብቻ… ሳይንስ በተሻሉ በሚባሉ ግለሰቦች አቋም ሊቀያየር የሚችል እውነትም መሆኑን አሳይቶን ያልፋል። መጀመሪያ አንስትያን ዩኒቨርስ ያለቀ ሊሰፋ፣ ሊለጠጥ የማይችል አርጎ ተቀብሎ ነበር። ቆይቶ ግን ዩኒቨርስ ተስፋፊ እና ተለጣጭ መሆኑ ሲገባው… የመጀመሪያውን እውቀቱን የህይወቴ ትልቁ ስህተት ነበር እስከማለት አስደርሶታል። 

 በሁለተኛ ደረጃ አንዳንድ ኢአማንያን አባታቸው አድርገው ሲጠሩት የምናየው ስቴቨን ሃውኪንግ የፒኤችዲ ቴሲሱን የሰራው በክሬሽኒስት እሳቤ ሲሆን በኋላ ነው ዘፍጥረትን ወደ አለመቀበሉ የሄደው። ይሄን የማነሳው ሳይንስም ግለሰቦችን ተንተርሶ ተለዋዋጭ መሆኑን ለማሳየትም ነው። አባት አንስታይንም ስለ ዩኒቨርስ በጥልቀት እንደተረዳ "ይሄ ነገርማ ንድፍ አውጪ አለው!" ከነሚለው አቋሙ ነው ይቺን ምድር የተሰናበተው። የይሆዋ ምስክር ወንድሞቻችን የሆኑ ሰዎች ንቁ መፅሄት ላይ እንደሚያካትቷት ተወዳጅ አምድ ማለት ነው። ለምሳሌ የእሳት ራትን ንድፍ ተገን ተደርጎ በተፈጠረው ላይት ኢሚቲንግ ዳዮድን (LED) እየጠቀሱ "ይሄማ ንድፍ አውጪ አለው!" የሚል ደስ የሚል ለሳይንስ የሚቀርብ ፅሁፍ "ንድፍ አውጪ አለው!" የሚል አምድ ስር አንብቤ አውቃለሁ። አንዳንድ ኢአማንያን እንደዚ ለመራመርም ንቁ ለማለት ነው :-D :-D 

 በአዲስ መስመር አንዳንድ ሃሳቦችን ደሞ እናንሳ…
 [፩] 
Universe began to expand from nothing (white hole) in the form of positive and negative energy (light and darkness)

 ኦሪት ዘፍጥረት ወ ሳይንስ ብዙሃኑ ሃይማኖት ዘፍጥረት ላይ ተመሳሳይ እምነት ስላለው እዛው ዘፍጥረት አካባቢ እንቆይ… አንድ ጤነኛ ኢኣማኒ "እንዴት እግዜር ከፀሃይ እና ከዋክብት በፊት፣ {ብርሃን ይሁን ብሎ}… ፀሃይና ከዋክብትን ዘግይቶ ፈጠረ? ይሄ አይጋጭም ወይ?" ብሎ በጨዋነት ሊጠይቅ ይችላል። በዚህ ተነስቼ እኔም ጥያቄ ልጠይቀው 

1) ይሄን ጥያቄ ማን እንዲመልስለት ነው የሚጠብቀው? አንድ ሃይማኖተኛ ካልመለሰለት፣ አጠቃላይ ሃሳቡ ስህተት እንደነበር ያረጋግጥለታል ማለት ነው? 
2) ጠያቂውም በራሱ መልሱ ካልመጣለት ጉዳዩ ስህተት መሆኑን ያረጋግጥለታል ማለት ነው? ጥያቄው ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት እስከመቼ ነው በይደር የሚያቆየው? የብዙ እልፍ አመታት ጥያቄዎቹን በራሱ ለመመለስ ምን ያህል አመት ይኖራል? 

 በዚ ጉዳይ ሃሳብ አንስቼ ወደ ሌላው ጉዳይ እናልፋለን… የሆነ ወቅት ላይ የነበሩ የሳይንስ ሰዎች… " ከፀሃይና ከከዋክብት በፊት ብርሃን ሊሆን(ሊኖር) አይችልም!" ብለው ዘፍጥረትን ፉርሽ አረጉት። ሰዉም የሚያውቃቸው የብርሃን ምንጮች እነሱው ናቸውና፣ ወደ ሳይንሱ ልቡ አመዘነ። ቆይቶ ሳይንስ ራሱ ፉርሽ ያደረገበትን ኅልዮት ቀይሮ "አዎ ፀሃይና ከዋክብት ከመኖራቸው በፊት፣ ብርሃን በphoton መልኩ ነበር" የሚል ሃሳብ ይዞ ተከሰተ። ያኔም ሳይንሱን ያመኑ ሰዎች "አሃ ሃይማኖቱም ልክ ነበራ!" ብለው ተመለሱ። እዚጋ በሳይንስ ዥዋዥዌ ላይ በዝምብሎ በማመን ለሚመላለሱ ሰዎች ጥያቄ እንጠይቃቸው… ሳይንሱ ሁለተኛውንም የመጀመሪያውንም ሃሳብ ይዞ ሲመጣ የሳይንስ አማኞች ለመቀበል ምንድነው መስፈርታቸው?… እንደወረደ በእምነት ብቻ የሚቀበሉት ከሆነ፣ ከሚተቿቸው ዝምብለው የሚያምኑ ሃይማኖተኞች በምን ተለዩ ታድያ?… ግድ ስለ ጉዳዩ በሚገባ ሊገባቸው አይገባም ወይ? ያውም ፕሩቭ ተደርጎ የሚዳሰስ ጉዳይ ሆኖ ማለት ነው። ወይንስ ሳይንቲስቶቹን እንዲሁ ስለሚያምኗቸው ነው? እዚጋ አንድ ነጥብ እንያዝና እንለፍ… ሃይማኖቱን ሳይገባው እንደሚቀበል ሁሉ ሳይንሱም ሳይገባው የሚቀበል አለ ማለት ነው። ይሄን ያነሳሁት አንዳንድ ኢአማኒ የቱጋር እንደቆመ ራሱን እንዲጠይቅም ጭምር ነው።

 [፪] 
አሁንም ዘፍጥረት ላይ ነን… የዘፍጥረት መጀመሪያ ስድስቱ ቀናት… እንደ ጥያቄም እንደ ሙድ እንደመያዝም (በዘፍጥረቱ ስድስት ቀናት) ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። "እግዜር በስድስት ቀን ተጣድፎ የሰራት ዓለም" እንደሚሉት፣ እንደመሳሰሉት ማለት ነው። ትልቁ ስዕል ግን ያ አልነበረም። ሆኖም በቀኖቹ ላይ ሁለት ነገር ላንሳና ወደ ትልቁ ስዕል እገባለሁ። አንደኛው ከያንዳንዱ የዘፍጥረት ክንዋኔ በኋላ "የመጀመሪያ ቀን፣ ሁለተኛ ቀን………" እያለ የሚቀጥለው (ቀን) የሚለው ቃል ነው። ይህን ቃል ኦርጅናሌው እብራይስጥኛ yom ነው የሚለው… ትርጉሙም ከ እስከ የሌለው፣ a period of something ማለት ነው… እንግሊዘኛው day እንደሚለው ማለት ነው። 

 In modern English, the word "day" has five meanings: 
1) Period of light between sunrise and sunset. 
2) The time (24 hours) that it takes the earth to revolve once on its axis. 
3) A period or era.
4) A time of power, glory, etc.
5) Daily work period (7 or 8 hours).

 በነገራችን ላይ የኛም ቀን ትርጉሙ ተመሳሳይ ይዘት አለው። ብርሃን ለሚታይበትም… ለሙሉ ቀኑም እንደምንጠቀመውም ማለት ነው። አንዳንድ ቋንቋዎች ሙሉ አይደሉም። ወይም ከሌላ የመጣን የሚገልፁበት ቃላት ላይኖራቸው ይችላል ብለን ነጥብ ይዘን እንለፍ። የሚቆጠረውን ቀን ስንል ግን የካላንደሩን ማለታችን ነውና ፀሃይን ማሰባችን አይቀርም። ፀሃይ ደግሞ በአራተኛው ቀን የመጣች ነችና ሙድ የምንይዝበትን ጉዳይ ኩም ታረግብናለች። 

 እጅግ የተወደዱ አባታችን አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ So Many Years with the Problems of People. Part I - Biblical Questions ላይ አንድ ጥያቄ ተጠይቀው የመለሱትን እንመልከት
 Question
 How can the saying of the Bible that God created the world in six days coincide with the opinion of the geologists that the age of the earth is thousands even millions of years? 

 Answer: 
 The days of creation are not Solar days as our days now. 

 The day of creation is a period of time, not known how long, which could have been a second or thousands or millions of years. This period was determined by the saying "so the evening and the morning were..." 

 The evidences for this are many, among which are: 
1. The Solar day is the period of time between the sunrise and its rising again or between the sunset and its setting again. Since the sun was only created on the fourth day (Gen. 1:16-19)., then the first four days were not solar days.
2. As for the seventh day, the Bible did not state that it has ended. The Bible did not say [so the evening and the morning were the seventh day], and thousands of years passed from Adam till now while this seventh day is still going on. Accordingly, the days of creation are not Solar days but unknown periods of time.
3. As a whole, the Bible said about all the creation and its six days: ". This is the history of the heavens and the earth when they were created, in the day that the LORD God made the earth and the heavens," (Gen. 2:4). 

So the Bible summed up in the word (day) all the six days of creation... Let the geologists say then whatever they want about the age of the earth; for the Bible did not mention any age for the earth that may contradict the views of the geologists. The way the Lord looks to the measurement of time is explained by the apostle as follows: "With the Lord one day is as a thousand years, and a thousand years as one day " (2 Pet. 3:8). 

 እዚጋ የአቡነ ሺኖዳን ለኢቮሉሽን ክፍት የሆነ ሃሳብ ተመልከቱ። በርግጥ እጅግ እጅግ የተለዩ ሰው ናቸው። አንድ የሃይማኖት አባት ነገሮችን በዚህ መልኩ ከተረዳና ከገለፀ አማኙም ኢአማኙም መጠየቅ ያለባቸው ጥያቄ እንዳለ አንስቼ ብቻ ልለፍ። 

ያም ሆነ ይህ ስንቀጥል ዋናው ጉዳይ ቁጥሩ ብቻ አለመሆኑን እናያለን! በስድስቱ ቀናት የተከናወኑት ነገሮች አሁን ካለው ሳይንስ ጋር ይጋጫሉ ወይስ አይጋጩም? ነበር ዋናው ጥያቄ መሆን የነበረበት… ኢቮሉሽኑ የሚያሳየው ግን ፍፁም ስምም እንደሆኑ ነው።
 በስድስቱ ቀናት የተከናወኑት… 
 Energy evolution
 Hydrogen evolution
 Planetary evolution
 Stellar evolution
 Biological evolution
 Intelligent evolution ናቸው። መቼስ መፅሃፉ ቃል በቃል እንደዛ ማለት እንደማይኖርበት ማሰቡ ቀላል ይመስለኛል። ምክንያቱም መፅሃፉ የተፃፈው ለሁሉም አይነት ዘመን ሰዎች ነው። ሳይንሱ ደግሞ እነዚህን ቃላት ያገኘው እጅግ ዘግይቶ ነው። እያስተዋልን ስንሄድ ጉዳያችን ሂደቱ አንድ እና አንድ አይነት መሆኑን መረዳታችን ነው።

 ከላይ ያለውን ሃሳብ በምሳሌ ስናየው ማለት የፈለኩት በደንብ ግልፅ ይሆናል። በመጀመሪያ የመፅሃፍ ቅዱሱን ሁለተኛውን የዘፍጥረት ቀንና የሳይንሱን ሁለተኛውን ኢቮሉሽን (Hydrogen evolution) በሁለቱም ቋንቋዎች እንየው… (ሁለተኛውን መጀመሪያ የመረጥኩት በምክንያት ነው፤ ሌሎቹን ቀጥዬ አመጣቸዋለሁ)… . 

ሁለተኛው ቀን በመፅሃፍ ቅዱሱ አገላለፅ…
[And God said, let there be a firmament in the midst of the waters, & let it divide the waters from waters. And God made the firmament, and divided the waters which were under the firmament from the waters which were above the firmament; & it was so. And God called the firmament Heaven. And there was evening & there was morning, second day.] 

 አሁን ደሞ ይሄ በሳይንስ ዘይቤ ቢገለፅ ምን ይመስላል የሚለውን እንይ… 
The Biblical model in modern popular scientific languague
[And God said: let the positive energy of photons be converted into clouds of Hydrogen plasma ("waters") & let vacuum space ("firmament") separete each Hydogen plasma cloud from all the others. And God created the space between the clouds of Hydrogen plasma both within and outside of each protogalaxy (future galaxy). And it was so. And God called the space Heaven. And a pur field of vacuum space arose ("there was evening") and clouds of Hydrogen plasma arose. ("and there was morning") : thus went the socond stage of creation of universe by the Absolutely Perfect God. We call this period of creation the stage of Hydrogen evolution ("second day"). 

የመጀመሪያው ቀንን እንይ ደግሞ 
[In the beginning God created the heaven and the earth. And the earth was without form, and void, and darkness was upon the face of the deep. And the Spirit of God moved upon the face of the waters. And God said, Let there be light: and there was light. And God saw the light, that it was good: and God divided the light from the darkness. And God called the light Day, and the darkness God called Night. And there was evening and there was morning, first day.'] 

ይሄንንም በሳይንስ ዘይቤ ቢገለፅ የሚለውን እንየው 
The Biblical Model in Modern Popular Scientific Language 
[1. In the beginning God created space, time, and everything which moves and develops in space and time. "In the beginning God created the heaven and the earth." 

 2. According to the ideal program of material development created by God, the Universe originated from nothing as a zero sum of postive and negative energy (the first stage of evolution, i.e., the "first day" of creation). But the original positive energy had not yet assumed the substantial form of weighty physical bodies. It consisted of an intact and weightless continuum of formless photons whose physical volume, weight, and rest mass were equal to ideal zero "The earth," i.e. matter, "was without form, and void." The negative energy gave rise to vacuum (i.e., physical!) space, which constitutes an unbroken continuum of antiphotons. This physical space expanded in an ideal void "And darkness was upon the face of the deep." The ideal (nonmaterial) program for the evolutionary developmet of matter outlined by God was already encoded in the foundations of this primordial Universe. According to this program, in the second phase of the evolutionary development of matter, the pure and weightless energy of the primordial Universe would subsequently be transformed into weighty clouds of hydrogen plasma "And the Spirit of God moved upon the face of the waters." 

 3. And God created an ideal program of energy evolution. This program constituted a combination of laws for the purely energetic world such as the law of the creation and conservation of energy "And God said, Let there be light." And the positive energy of photons was born from nothing "And there was light." According to the law of conservation created by God, this event was simultaneously accompanied by the generation of the exact same amount of negative energy, from which vacuum space expanding from zero was formed. 

 4. Thus God split an ideal zero into a zero sum of material opposites, namely positive and negative energy "And God divided the light from the darknes." And God was satisfied with the results of this creation, because it included weightless and formless photons which would be transformed into weighty substance with volume "And God saw the light, that it was good." 

 5. And God called the positive energy of the photons light ("day") and the negative energy of vacuum space dark ("night"). And both expanding space ("and there was evening") and energetic photons ("and there was morning") were born. Thus, the first stage of the creation of the Universe by the absolutely perfect God was completed. We call this period of creation the stage of energy evolution "the first day."]

ሶስተኛው ቀን 
[And God said, Let the waters under the heaven be gathered together unto one place, and let the dry land appear: and it was so. And God called the dry land Earth, and the gathering together of the waters God called Seas: and God saw that it was good. And God said, Let the earth bring forth grass, the herb yielding seed, and the fruit tree yielding fruit after its kind, whose seed is in itself, upon the earth: and it was so. And the earth brought forth grass, and herb yielding seed after its kind, and the tree yielding fruit, whose seed was in itself, after its kind: and God saw that it was good. And there was evening and there was morning, third day.'] 

በሳይንስ ዘይቤ ሲገለፅ…
The Biblical Model in Modern Popular Scientific Language
[And God said: let one of the clouds of hydrogen plasma in the Galaxy be condensed so that planets separate from it. And it was so. And God called one of these planets Earth, and God called those depressions on the earth into which water subsequently flowed the oceans and the seas. And God saw that the earth was suitable for life. And God said: let the earth acquire the "seeds of biological life" from which different species of plants, namely grass, the herb yielding seed, and the fruit tree yielding fruit after its kind will later grow. And it was so. And the earth subsequently produced different species of plants from those "seeds of biological life" which it had inherited from the cosmos. Each plant was born from a seed, developed, matured, yielded seed after its own kind, aged, died, and was then reborn from a seed. And God was satisfied with the results of his creation. And the earth formed ("and there was evening") and plants appeared on it ("and there was morning"): so went the third stage of the creation of the Universe by the absolutely perfect God. We call this period of creation the stage of planetary evolution ("third day").]

አራተኛው ቀን 
[And God said, Let there be lights in the firmament of the heaven to divide the day from the night; and let them be for signs, and for seasons, and for days, and years. And let them be for lights in the firmament of the heaven to give light upon the earth: and it was so. And God made two great lights, the greater light to rule the day, and the lesser light to rule the night: God made the stars also. And God set them in the firmament of the heaven to give light upon the earth. And to rule over the day and over the night, and to divide the light from the darkness: and God saw that it was good. And there was evening and there was morning, fourth day.] 

በሳይንስ ዘይቤ ሲገለፅ…
The Biblical Model in Modern Popular Scientific Language 
[And God said: Let there be luminaries in heaven and let them be set in relative motion so that winter and summer, day and night may alternate with each other. Celestial bodies must be in periodic motion so that time can be reckoned by them and one era can be distinguished from another, one season can be distinguished from another, and day can be distinguished from night. And let the stars, the sun, and the moon be luminaries in celestial space so as to shine upon the earth, and it was so. And God made two great luminaries: a larger luminary to rule the day, and a smaller luminary to rule the night and the stars. And God arranged them in space so that their relative motions would make it possible to illuminate and heat the surface of the earth. And so that the seasons of the year (winter and summer) and days and nights would alternate with each other. And God was satisfied with the results of his creation, because within themselves they contained all the conditions necessary for the next stage of the evolutionary development of the Universe, namely the stage of biological evolution. And the stars twinkled ("and there was evening") and the sun shone ("and there was morning"): Thus went the fourth stage in the creation of the Universe by the absolutely perfect God. We call this period of the creation of the Universe the stage of stellar evolution ("fourth day").]

አምስተኛው ቀን 
[And God said, Let the waters bring forth abundantly the moving creature that hath life, and fowl that may fly above the earth in the open firmament of heaven. And God created great whales, and every living creature that moves, which the waters brought forth abundantly, after their kind, and every winged fowl after its kind: and God saw that it was good. And God blessed them, saying, Be fruitful, and multiply, and fill the waters in the seas, and let fowl multiply in the earth. And there was evening and there was morning, fifth day.] 

በሳይንስ ዘይቤ ሲገለፅ…
The Biblical Model in Modern Popular Scientific Language 
[And God said: let the fish first appear in the water and then the birds in the skies above the earth. And God first created living creatures in the water, then the large fish and marine animals, and then God created the winged birds which fly through the air. All of them were born, developed, matured, produced offspring after their kind, aged, died, and were born again. And God was satisfied with the results of this creation, because the biological systems contained all the conditions necessary for the next stage of the evolutionary development of the Universe, namely the stage of intelligent evolution. And God blessed them, saying: be fruitful and multiply and fill the water in the seas and the space above the earth. And thus fish arose ("and there was evening") and the birds arose ("and there was morning"): thus went the fifth stage of the creation of the Universe by the absolutely perfect God. This period in the evolution of the Universe is what we call the stage of biological evolution: ("fifth day").]

ስድስተኛው ቀን 
[And God said, Let the earth bring forth the living creature after its kind, cattle, and creeping thing, and beast of the earth after its kind: and it was so. And God made the beast of the earth after its kind, and cattle after their kind, and every thing that creeps upon the earth after its kind: and God saw that it was good. And God said, Let us make a human being in our image, after our likeness: and let them have dominion over the fish of the sea, and over the fowl of the air, and over the cattle, and over all the earth, and over every creeping thing that creeps upon the earth. 

So God created a human being in God's own image, in the image of God were they created, male and female. And God blessed them, and God said unto them: Be fruitful, and multiply, and replenish the earth, and subdue it, and have dominion over the fish of the sea, and over the fowl of the air, and over every living thing that moveth upon the earth. And God said, Behold, I have given you every herb bearing seed, which is upon the face of all the earth, and every tree, in which is the fruit of a tree yielding seed; to you it shall be for to eat. And to every beast of the earth, and to every fowl of the air, and to every thing that creepeth upon the earth, wherein there is life, I have given every green herb for to eat, and it was so. And God saw everything that God had made, and, behold, it was very good. And there was evening and there was morning, sixth day.']

በሳይንስ ዘይቤ ሲገለፅ…
The Biblical Model in Modern Popular Scientific Language 
[And God said: let the different species of living creatures multiply on the earth: and creeping things after their own kind, cattle after their own kind, and the beasts of the earth after their kind. And it was so. And God created the beasts of the earth after their own kind, cattle after their own kind, and all the creeping things of the earth after their own kind. All of them were born, developed, matured, produced offspring after their own kind, aged, died, and were born again. And God was satisfied with the results of this creation, because God had created all the conditions necessary for the appearance of a special living creature on the earth, namely a human being, who possesses high intelligence and creative abilities. 

And God said: let us create a human being after our own image, after our likeness, and let them have dominion over the fish of the sea, and over the fowl of the air, and over the cattle, and over all the earth, and over every creeping thing that creeps upon the earth. And God created a human being after God's own image and likeness. And humans appeared on the earth as the relative likeness of the absolute Creator, as the material image of the nonmaterial God, and as the inseparable unity of sexual opposites, male and female. And God blessed them and said to them: be fruitful and multiply and replenish the earth and subdue it, and have dominion over the fish of the sea, and over the fowl of the air, and over every living thing that moves upon the earth. And God said: I, God, have created the primal seeds of different plant species from which shall grow seed-bearing herbs and fruit trees, which shall multiply over the entire earth from year to year. These plants, the herbs, vegetables, and fruits of the trees shall be plant food for humans. Other species of animals shall also live on plant food: all the animals of the earth, all the birds in the sky, and all the creeping animals. And it was so. And different species of animals arose on the earth ("and there was evening"), and humans arose ("and there was morning"): thus went the sixth stage of the creation of the Universe by the absolutely perfect God. We call this period of the creation of the Universe the stage of intelligent evolution: the sixth day. And God was satisfied with the results of all of this creation, because in the person of man and woman God had created worthy helpers who was capable (like God) of creating purposefully and consciously. ("And God saw every thing that God had made, and, behold, it was very good.")]

  እስቲ በደንብ እዩዋቸውና…መፅሃፍ ቅዱሱ የተፃፈው ለሁሉም አይነት ሰዎች እና ለሁሉም ዘመን ሰዎች መሆኑን አስቡ። ሳይንሱ ግን ለምን ያህሉ ግልፅ ነው? ምናልባት ሙሴ በፃፈበት ሰዓት ሃይድሮጅን ፕላዝማን የሚያውቅ መኖሩን እንጃ… ያው መደምደም ስለማልፈልግ ነው እንደዛ የምለው። ሙሴ በኖረበት በቀስትና ደጋን ዘመን ሃይድሮጅን ፕላዝማ ብሎ ማሰብ ራሱ የማይታሰብ ነው። ውሃን ግን ስናየው ሁሌም አለ። ውሃ ደግሞ የሁለት ሃይድሮጅን እና አንድ ኦክስጅን ውጤት መሆኑን አሁን እናውቃለን።… ስለዚህ ነገሮች ሁሉ እንዲህ ሰፋ ባለ መነፅር ሲታዩ ይጋጫሉ ያልናቸው ነገሮች ሳይሆን… የሚጋጨው የኛ ቁንፅል ዕውቀትም ሊሆን ይችላል ማለትም እንችላለን። ዋናው ነጥብ አስፍተን እያየንም እንሂድ ነው። 

 [፫] 
ወደ ብዙ ጀማሪ ኢኣማኒያን ሙድ መያዣ ወደሆነው ወደ ኖህ መርከብ ሄደን ጥያቄ ጭረን እንቀጥላለን። በኢአማንያኑ ዘንድ የኖህ መርከብ ብዙ ቀልዶች የሚፈጠርበት ቦታ ነው። አብዛኛውም ያዝናናል። ግን በብዛት የቀልዶቹ መነሻ (ትላንትን በዛሬ መነፅር ማየት) መሆኑን እንደርስበታለን። አለማችን በብዙ ነገር ተለዋውጣለች… ጂኦግራፊ ስንማር pangea እና ኢንተርኮንቲኔንታል ድሪፍትን ማሰብ… እይታን ሰፋ ለማረግ ይረዳል ብዬ አስባለሁ። አብዛኛው የኖህ መርከብን ሲያስብ የሚያስበው አለም አሁን ያላትን ቅርፅ ነው። ያ ለትልቅ ስህተት ይዳርጋል። አለም አሁን ያላትን ሁኔታ የያዘችው ብዙ ነገሮችን አልፋ ነው። ባዮሎጂ ስንማርም ስለ animal kingdom, family የተማርናቸው ነገሮች እንደ ጂኦግራፊው ሁሉ ነገሮችን ሰፋ አድርጎ ለማየት ይረዳናል። እንኳን የሩቁ የቅርብ የምናቃቸው ወንዞች እንኳን ደርቀው ሜዳ ሆነዋል።

 [፬] 
ኢአማንያን ከምንም ነገር መና መውረዱ ይገርማቸዋል። አብዝተው አብዝተውም ሙድ ይይዛሉ። እንዴት እንዴት እያሉም ይገረማሉ። ግን ቀድመው በመና የተገረሙት እዛው መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ። እና መገረሙ የሚገርም ነገር የለውም ማለት ነው። መፅሃፉ ይላል… "እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት:– እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ’ን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን" በጣም ነው የሚገርመው። እኔም እግዜርን ብዙ ጊዜ አምቼው አውቃለሁ። የላይኛውን ጥቅስ ደግሞ ቃል በቃል ነው እኔም ያማሁት። በግሌ ዝምብዬ የማምን ሰው አይደለሁም። እንደ ቶማስ መዳሰስ እፈልጋለሁ። ያ ተፈጥሮዬ ነው። ይሄን የፈጠረኝ ያውቀዋል ብዬ ስለማምን እግዜርን ባማውም ልቤ ዝግ አይደለም። መልስ ሲያገኝ "አሃ ይሄም አለ" ብሎ ምልስ ይላል ልቤ። እዛው መዝሙር 77 ላይ ወረድ ብሎ እንዲህ ይላል። <<ከሰማይ የምስራቅን ንፋስ አስነሳ÷ በኃይሉም የደቡብን ነፋስ አመጣ ሥጋን እንደ አፈር÷ የሚበሩትንም ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፤ በሰፈራቸው መካከል÷ በድንኳናቸውም ዙሪያ ወደቀ>> እዚጋ ተገረምኩ። ከዚ በፊት እግዜርን ያማሁበት ነገር መልሱ ተመለሰልኝ። ከላይ ያለው ንፁህ ሳይንስ ነው። ምንም አይነት ውሃ በሌለበት ቦታ ላይ አሳ የሚዘንብበትን ሳይንሳዊ ምክንያት፣ በነፋሳት እንቅስቃሴ ነው የሚወሰነው። ከላይ ምስራቅና ደቡብን ልብ ይሏል። ይሄ መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ይኖራል የሚል ግምቱ አልነበረኝም። ለነገሮች ዝግ ስላልነበርኩ በጊዜ ፈቃድ አገኘሁት። እግዜርን ወደላይ ቀና ብዬ "ትገርመኛለህ እኮ!" አልኩት። እንዲህ ነው እኔና እግዜሩ የምንግባባው። በፈጠረኝ ልክ እንዲያሳምነኝ ነው የምፈልገው። ስለሚያውቀኝ ባማውም፣ ብጠይቀውም፣ ብጠራጠረውም ከክፉ አይቆጥርብኝም። 

 [፭] 
በዛ ያለ ኢአማኒ ሃይማኖት ነው ደሃ ያረገን ይልና ራሱ ደሃ ሆኖ ታገኘዋለህ። በርግጥ ሃይማኖት እና የስራ ባህል የሚገናኙባቸው መስመሮች እንዳሉ አይካድም። ግን ሃይማኖቱ ለዚ ቀጥታ ተጠያቂ አይሆንም። ብዙ ጊዜ ለዚህ የሚወቀሱት የአብርሃም ሃይማኖቶች ናቸው። ግን ሰፋ አረገን ካየነው እነ ቻይናን መሰል የእስያ አገራት እጅግ ደሃ አገራት ነበሩ። ስለ አብርሃምም ከነአካቴው ማወቃቸውን እንጃ። ከዛ ተለወጡ። የተለወጡት ግን ሃይማኖት ትተው ወይም ቀይረው አይደለም። ከሆነ እንኳ የአብርሃሙን አይደለም። ሰፋ ለጠጥ አርገን እንይ ለማለት ነው። 

 [፮] 
ብዙ ጊዜ አንድ ኢአማኒ ሃይማኖተኛ ሲያይ የሚሰማው ስሜት በግርድፉ ተመሳሳይ መሆኑ ይገርመኛል። እይታው (የማፌዝና የመናቅ ስሜት) እንዳለበት እንዲሁ ያስታውቃል። ይሄ እዚህ አገር ብቻ ሳይሆን ድንበር ተሻጋሪ ነው። ምክንያቱ በአግባቡ ያልተገራ እብሪት ይመስለኛል። ግን እርግጠኛ አይደለሁም። ሆኖም እዚህ ጋር ያነሳሁት ቀጥሎ ለማነሳው ሃሳብ ስለሚረዳኝ ነው። አንድ ኢአማኒ ወደ አማኒነት ሲመለስ በበዙ ኢአማንያን ዘንድ የሚፌዝበት ምክንያት ከላይ ያለችዋ እብሪት ነች። በዚህም የተነሳ ከኢአማኒነት ወደ አማኒነት የተመለሱ ሰዎች በድፈረት አያወሩም። ዝምብሎ ማመን ምክንያታዊነትን ማጣት ተደርጎ ይሳላል— ብዙ ጊዜ። ይሄ ግን ትክክል አይደለም። 

ሁለት ነገር እንይ… 
 1) በማመን ብቻ ተመለስኩ የሚለውም ምን እንደገጠመው በትክክል ሳንረዳ ምክንያታዊነቱን እንዳጣ መቁጠር ፍፁም ትክክል ነው ብዬ አላስብም። ለምሳሌ ህልም አይቼ ተመለስኩ የሚል ሰውን በምን አይነት ሳይንሳዊ መንገድ ነው ትክክል አለመሆኑን የምንረዳው? ስለ ህልምስ ምን እናውቃለን? ሳይኮ አናሊስቱ ፍሮይድ ነው dream analysis ብሎ በድፍረት የፃፈው፣ ልክ መሆኑን ምንድነው ማረጋጋጫችን? … በተአምር ተመለስኩ ያለውንም ትክክል አለመሆኑን የምናሳይበት መለኪያ ምንድነው?
 2) ጥቂት የማይባሉ ኢአማንያን ደሞ አሉ… ኢአማንያኑ በሚፈልጉት መንገድ፣ መርምረው መርምረው፣ ስንትና ስንት ዶሴ አገላብጠው… ላባቸውን ጠብ አርገው በምክንያት መልሰው አማንያን የሚሆኑ። በግለሰብ ደረጃ ቶልስቶይን ማንሳት እንችላለን። በሁለቱም በኩል የሚሰራ ነው የቶልስቶይ ጉዳይ። በማሰብ ውስጥም በህልምም በኩል ማለቴ ነው። ህልም ላይ በጣም ኩሪየስ ነኝ በግሌ። ስደጋግመው ልብ ያለ ያስተውለው ብዬ ነው። ከብዙ ብዙ አመት በኋላ ስለ ህልም የደረስኩበትን ለሰው አካፍላለሁ። ለዛ ያብቃኝ ብዬ ልለፍ። በነገራችን ላይ አማንያን ስል ግድ የሃይማኖት ተቋም ውስጥ ያሉ ማለቴ አይደለም። በፈጣሪ ህልውና ማመን የሚለውን ብቻ ያዙልኝ። ቶልስቶይን ከልጅነት እስከ ዕውቀቱ በሰፊው ስለተፃፈ ልለፈውና… የሚዳሰስ ምሳሌ ላንሳ።

 አንድ ኢኣማኒ ወደ አማኝነት ሲሄድ የሚሄድበት ርቀትን ለማሳየት አንድ ፊልምን ማንሳት፣ ከላይ ላነሳሁት ሃሳብ በሚገባ ምስል ከሳች ይሆናል ብዬ አስባለሁ። The case for Christ የ2017 ፊልም ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ፊልም ነው። ሶስት ነገር እናይበታለን ፊልሙን።
 1) አንድ ሰው ኢአማኒ ሲሆን የኢአማኒ እይታውን
 2) አንድ ኢአማኒ አማንያንን የሚያይበትን መነፅር
 3) ምናልባት ከተመለሰ… ምን ያህል ርቀት ሄዶ እንደሚመለስ… ስንት ዶሴ እንደሚያገላብጥ… ስንት አይነት ጥያቄዎች እንደሚመልስ… ለማጣራት የት ርቀት ድረስ እንደሚሄድ… ላቡን እንዴት ጠብ አርጎ እንደሚፈጋ ፊልሙ በደንብ ያሳያል። የትኛውም ኢአማኒ በነዚህ ሶስት ነገሮች የሚታቀፍ ይመስለኛል። ==> አሁንም አላማዬ ነገሮች ስለሚታዩበት መንገድ ብቻ እንጂ… ሰውየው ተመለሰ አልተመለሰ ጉዳዬ እንዳልሆነ ስገልፅ፣ ነጥቤን በማስታወስ ነው። የዚ ብሎግ አላማ ስብከት አይደለም። ኢአማንያን በዚ መልኩ ነገሮችን ብትሾፏቸውስ እንደማለትም ነው። 

 በስተመጨረሻም… አንድ ሰውዬም ትዝ አለኝ… Francis Colling ይባላል…the languague of God የሚል መፅሃፍ አለው። ስለ DNA የተፃፈ አሪፍ መፅሃፍ ነው። በአማርኛም እንደተተረጎመ አውቃለሁ። ያነሳሁት ግን ለዛ አይደለም። ከኢኣማኒነት የተመለሰ ሰው ነው። ኢኣማኒ እያለ… አንዴ ክሊንተን ፕሬዚዳንት እያለ፣ ስለ እግዜር ሲያወራ ገርሞት፣ የተሰማውን የተናገረበት መንገድ ስላስገረመኝ ነው። "አንድ ነፃ አገር የሚመራ ሰው፣ እንዴት እግዜር ምናምን አይነት ገተታ ይጫወታል" … ቃል በቃል ባይሆንም እንደዚ ነው ሃሳቡ። ይሄን የፃፈው ከተመለሰ በኋላ እንደ ኑዛዜ ነው። አብዛኛው ኢኣማኒ እንደዛ የሚሰማው ይመስለኛል። እናም ኖርማል ነገር ነው ለማለት ነው። የተሻሉ ብሎ ከፍ ያረጋቸው ሰዎች ሃይማኖተኛ ሲሆኑ ይገርሙታል። ለምን ብሎ ግን መጠየቁን ረስቶታል። በሳይንስም የሚያምኑ አማንያን እንዳሉ ስለተረሳ ለማስታወስም ነው። 

 ማሳረጊያ… ጤነኛ ኢኣማኒ እዛም እዚም ብሎ የተለያዩ ሃሳብ ያስተናግዳል እንጂ… የሰዎች ሃይማኖትን በመሳደብ፣ በማንጓጠጥ ራሱን አይገልፅም። የሰዎችን ሃይማኖት በመሳደብ ራሱን የሚገልፅ ኢአማኒ፣ መነሻው ጥልቅ ምክንያታዊነት ሳይሆን፣… በጥልቀት ውስጡ ባላወቀው ሰአት የተፈጠረ የስነልቦና መቃወስ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። የሆነ የችግሩ ሰአት ላይ ፈጣሪ ብሎ ያሰበው አምላክ አልደረሰልኝም የሚል ውስጣዊ በቀል ሊሆን ይችላል። ሃይማኖቱን እና ሃይማኖተኞቹን በመተቸት፣ በመዝለፍ ውስጡ ይረካለታል። ይሄ በሽታ ነው። ጤነኛ ኢአማኒ የሰዎች የሆነን ሁሉ በማክበር የኔ የሚለውን በመፈለግ የሚተጋ ነው። የኔ የሚለው ላይ ተመራምሮ ካልደረሰ የሰዎችን የሚነቅፍበት አንዳች ምክንያት እንደሌለው፣ በምክንያታዊነት በሚታመን ልቡ መታመን አለበት ብዬ በፅኑ አምናለሁ።
iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

2 comments:

  1. ለዚህ ፅሁፍ መልስ ለመስጠት ባልዘጋጅብትም ፀሃፊዉ ኢአማኒ የሚለዉን አካል በሃይለ ቃል የተቸበት መንግድ ግን ከአንድ ሎጂካል ናኝ ብሎ ኢአማኙን ዞር ብሎ እንዲያ ካሰበ ፀሃፊ የሚጠበቅ አይምስልም ምክንያቱም ጸሃፊዉ መጀመሪያዉኑ ኢአማኙን ለመተቼት እንደመነሻ የወሰደዉ እርሱ የሚያምንበትን ሃይማኖት መፅሃፍ ብቻ በማጣቀስ በመሆኑ ከ 4000 በላይ ሃይማኖቶችን ግንዛቤ ዉስጥ ሳያስገባ biased ሆኖ መፀሃፍ ቅዱስን ለኢአማኙ አስረድቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አንድ ኢአማኝ ከመጀመሪያዉ ስለ ትክክለኛነታቸዉ የሚነሳዉ የሃይማኖት መጽሃፍት ላይ ነዉ፤ፀሃፊዉ መፅፍ ቅዱስን እያጣቀሰ ሲያስረዳ በመጀመሪያ መፅሃፍ ቅዱስ ትክክለኛ ስለመሆኑና ከየት እንደመጣ መንደርደሪያ ማስቀመጥ ነበረበት(ምርጥ ድርሰት ነዉ የሚል እምነት ያላቸዉ ቀላል አይደሉምና)፡፡ በሌላ በኩል ኢአማኝ በመባል የሚገለፁት ሁሉን የሃይማኖት አስተምሮ መፅፍት የማወቅ ግዴታ ያለባቸዉ አይመስለኝም ምክንያቱም ጥክለኛዉ ሃይማኖት የትኛዉ ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ሲያቀርብ ከ4000 በላይ የተለያየ መልስ የሚሰጠዉ ከሆነ ቆም ብሎ የራሱን ወስኖ ማለፍ ያለበት ይመስለኛል ለምሳሌ እኔ የትኛዉንም ሃይማኖት ሳልከተል ነገር ግን ፍጥረተ ዓለሙን የፈጠረ አንድ ሃይል እንዳለ በመረዳት ከሃይማቶች ግን በጎ እሴቶችን ተቀብዬ መኖር የምችል ቢሆንም በብዙሃኑ ግንዛቤ ግን ሃይማት የሌለዉ ወይም በፀሃፊ አገላለፅ ኢአማኒ የሆነ ግለሰብ በጎ እሴቶችና ተግባራት ሊኖሩት እንደማይቸሉ ይታመናል አማኞች ከኢአማኞች በላይ የሚፈፀሙት ቆሻሻ ተግባር ግን ግለሰባዊ ድርጊት ተደርጎ ይታለፋል፡፡

    ReplyDelete
    Replies

    1. ወንድሜ በቅድሚያ ስለመዘግየቴ ይቅርታ ኢንተርኔት ከነ አካቴው የማልጠቀምበት የራሴ ብዙ ወራት ስላሉኝ ነው። በመቀጠል ስለ አስተያየትህም በእጅጉ ጎንበስ ብዬ አመስግኛለሁ።

      ቀናነት ያየሁብህ ስለመሰለኝ ነው የምመልስልህ። ያነሳኸው ጉዳይ ብዙ የተባለ እና የተለመደ ነው። የምሰጥህንም አስተያየት በቀናነት ውሰደው።

      1) የፃፍኩትን በሙሉ በፃፍኩበት መንፈስ አላነበብከውም። ደግመህ ሙሉውን ማንበብ ይኖርብሃል። ስለ ኢአማንያን እንዴት አግዝፌ እንደፃፍኩ በዛው ትረዳለህ።

      ይሄ መግቢያዬ ነበር....
      [[[[ (ጤናማ ኢኣማኒነት፣ ሰው ተፈጥሮን (ስነ ፍጥረትን) የሚያስስበት አንደኛው መንገድ እና ሰፊ ልብ ያለው ሰው ዘው ብሎ የሚገባበት ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ። አምኜም እቀጥላለሁ!) 
       (ኢጤናማ ኢኣማኝነት እንደሚታየው ኢ-ኢ ይበዛዋል) የሌሎች ሁሉ ስህተት ነው ብሎ ደምድሞ ስለጀመረ፣ ጥረቱ ሁሉ ያንን ፕሩቭ ፍለጋ ነው። ብዙ ጊዜም አቋቋሙ፣ ከተማሳሳይ ሃሳብ ካላቸው ጋር ብቻ ሲሆን ታዝበናል። ለአዲስም ሀሳብ ዝግ ነው) አንዳንዶቻቹ ግን እንደዛ አይደላቹምና የሚከተለውን ልላችሁ ወደድኩ (ቴዎፍሎሶች ሆይ ብዬ ልጀምርልህ እንዴ? :-D ) 

       ከኔ በተቃራኒ የቆመ ሃሳብ ሳገኝ ነው፤ እኔ በራሴ የቆምኩበት ሃሳብ እንዳለኝ የሚሰማኝ። ስለዚህ የተለየ ሃሳብ ጥግ ድረስ አድናቂም ወዳጅም ነኝ፤ በምንም ጉዳይ ላይ። እና የኢኣማንያን ጥያቄዎች ያብቡ፣ ይለምልሙ፣ ይብዙ ባይ ነኝ። ሆኖም አንድ ጤናማ ኢኣማኝ ጥያቄው (የቢሊየን አመታት እንደመሆኑ መጠን) መልሱን ሁሉ ከአንድ ወቅት፣ ከአንድ ሰው (ተቋም)፣ ከአንድ አይነት መስመር ብቻ (ለምሳሌ ንባብና ማሰብ) ከጠበቀ ምኑን ኢኣማኒ ሆነ? ምኑን ሰፊ ልብ ኖረው? ወደ ጉዳዬ እየተንደረደርኩ ነው… 

      ዛሬ የማነሳው ሃሳብ፣ የማንንም ጥያቄ ለመመለስ አይደለም። ሰዎች በተለየ ሁኔታ ካዩት ነገር ይልቅ፣ እንዲህም ቢያዩት የሚለውን ስሜት ለማንፀባረቅ ነው። ሰው ካየው ነገር ይልቅ በሚያይበት መንገድ መሄድ አንዳንዴ ጥሩ ነው። ጥሩ ነው ብለንም እንቀጥል። ጀመርኩኝ… ]]]]]

      አየህ? አንተ ባልከው መልኩ ኢአማንያንን አልገለፅኩም። መከፋፈሌንም ልብ በል።

      2) የብዙ ሃይማኖቶች መነሻ የአብርሃም እምነቶች ስለሆነ የሚል ሃረግ ተጠቅሜያለሁ። ዳታ ጥሩ ነው። እኔም አንድ በሳይንስ እንደሚያምን ሰው በዳታ አምናለሁ። አንዳንድ ቁጥሮችን ግን እንደወረደ መውሰድ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የምናወራው ጉዳይ መሰረታዊው ላይ እስከሆነ ድረስ 4000 5000 6000 እያለ ሊቀጥል እንደሚችል አንተም አይጠፋህም። ስለዚህ ሁሉም ጋር መድረሱን ከጊዜ አንፃር አልሞክረውም። ስለ አብዛኛዎቹ ግን ልትገምተው ከምትችለው በላይ መረጃ አለኝ። በብዙ አመታት ከራሴ ጋር የቆየሁበት ዋነኛ ጉዳዬ ስለነበር። አሁን ፋይል ዘግቼ በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ነኝ ከራሴ ጋር። ፋይል የሚያስከፍት ጉዳይ እስኪገጥመኝ ድረስ።

      3) መፅሀፍ ቅዱስ ምርጥ ድርሰት ነው ብሎ የደመደመ ኢአማኒ ሲጀመር ይሄን ማንበብ አይገባውም። ለንደዚህ አይነት ኢአማኒም ፅሁፉ አልተፃፈም። ፍለጋው ሌላ ቦታ ነው መሆን ያለበት። ጊዜውን ከማጥፋት የተለየ ነገር አይሰጠውም። ነገሮችን ክፍት አርጎ የሚያይ ግን ቢያንስ የሆነ እይታ ይጨምርለታል ብዬ አስባለሁ።

      ግን ያንተን ሃይማኖት ባልከኝ መሰረት መነሻዬ የነበረው የአብርሃም እምነቶችን ሳይንስ ከሚለው ዘፍጥረት ጋር ይጋጫሉ ወይ? የሚለውን ለማሳየት ነው። አብዛኛውም የፅሁፉ ክፍል በዛ ዙሪያ ነው። ካልኩት ተነስተህ ይጋጩብኛል ካልከኝ እንዴት ብዬ ለመስማት ልቤ በደስታ ነው የሚከፈትልህ። ካልኩት ባትነሳም የተለየ አንግል
      ካለህ በደስታ ነው የምቀበልህ። ስለራሴ ብዙም ያወራው ስላልመሰለኝ ነው። የብዙሃኑ ነው ብዬ የተነሳሁትና!

      4) ድፍን 8 አመታት ኢአማኒ ሆኜ ኖሬያለሁ። ያንተን ሁኔታ እረዳለሁ። የኔ የሚለየው በሃላል እሰብክ ሁላ ነበር። ፍቅር፣ ነፃነትና ተፈጥሮ የተሰኙ የራሴ ስላሴዎች ነበሩኝ። አለምን በነዚህ መነፅር ውስጥ እየቃኘሁ ፍለጋ ውስጥ ነበርሁ። ያኔ ባልተሟላ መረጃ ያሳሳትኳቸው ብዙ ነፍሶች ነበሩ። ዛሬ እኔ ባለኝ ከትላንት የተሻለ መረጃ አቋሜን አስተካክያለሁ። ትላንት መሰናከያ ምክንያት የሆንኳቸው ውስጥ እንደተጣመሙ የቀሩ አሉ። ያ እጅግ ይፀፅተኛል።

      ወንድሜ ምን ይገርመኛል መሰለህ... ኢአማኒ ሆነው እንደ ከብት የሚኖሩ ሰዎች... ማነኝ ምንድነኝ ወዴት እሄዳለሁ... የማይሉ ኢአማንያን በእጅጉ ይገርሙኛል። እነ አብርሃም እንኳ የፀሃይ አምላክ ተናገረኝ እያሉ ኀሰሳ ወጥተው ነበር። ሰው እንዲህ ኢአማኒ ሲሆን የራሱ የሚለው የሆነ ድምዳሜ ላይ መድረስ አለበት። አልያም በፍለጋ እንደታተረ እድሜው ማብቃት አለበት ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ዝም ብሎ አለማመን ፈሪነት ነው የሚል አረዳድ አለኝ። ሰው መጠየቅ አለበት። ጥያቄው ደግሞ ወደ መልሱ ይወስዳል።

      እናም አንድ ቀን በመንገድ እንገናኝ ይሆናል። በፍለጋ መንገድ ማለቴ ነው። ኢአማኒም እያለሁ ደምዳሚ አልነበርሁም። አሁን በሃይማኖት ሆኜም ደምዳሚ አይደለሁም። በፅሁፍህ ቀናነት ተሰምቶኝ ነው እንዲህ ረዥም መፃፌ። ለምን ተሰማኝ አልልም። ሲሰማኝ መቀበል ነው። የሚያስቸኩል ነገር የለምና የቆምክበትን ደጋግመህ ፈትሽ ወንድሜ። እኔም እንደዛ እያደረግሁ ነው። በመንገድህ ቆሜ ስለነበር ስሜትህ ይገባኛል። ምናልባት እድሉን ተጠቅሜ ይሄን ማለቱ ስሜት ስለሰጠኝ ነው። አንዳንድ ቀን “ተሳስቼ ይሆን? ድምዳሜዬ ልክ ላይሆን ይችል ይሆን?” እያልቅ ቆም ማለት ጀምር። በመንገድህ ስለነበርሁ በልምድ የምሻልህ ስለመሰለኝ ነው። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። ማንንም እንዲህ ብዬ አላውቅም።

      በተረፈ መስመር በመስመር ጊዜ ወስደህ፣ ተዘጋጅተህ በፃፍኩት ዙሪያ አልያም ጨምረህ ብትፅፍልኝም መርጬ በደስታ አነብሃለሁ። በጣም በጣም በጣም በጣም አመሰግናለሁ። ደስ ብሎኛል።

      Delete

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement