Komentar baru

Advertisement

Still writing

Eriyot Alemu
Apr 4, 2022
Last Updated 2023-08-21T21:36:51Z
Advertisement

አዳም ረታ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ መፅሃፉ ላይ "የስብሐት ጢም" የተሰኘ እጅግ የምወደው ስራ አለው። ያው የሚያወራው ስለ ድርሰት፣ ደራሲነት እና ሐበሻዊነት ነው። እዛ ላይ የስብሐት ሚስት ገፀባህርይን የተላበሰችው ፋኖስ የሚፅፉ ሰዎች ለምን እንደሚፅፉ ግራ ይገባታል መሰለኝ። ይሄ የብዙ ፋኖሶች ጥያቄም ነው ብዬ እገምታለሁ። መልሱ ግን አጭር አይደለም። አዳም ረታ በሚገርም ሁኔታ ሊመልሰው ሞክሯል። ረቀቅ ባለ መንገድ… ሁሌም አዳምን ስገልፀው "የምታደንቀው ሰው ብቻ ሳይሆን የምትፈልጠውም ሰው ጭምር ነው!" የምለው በምክንያት ነው። 


በሌላ ቦታም Dani Shapiro የተባለች ሰው አለች። እነ ፋኖስ "አሁንም እየፃፍሽ ነው?" እያሉ ሲያማርሯት ይመስለኛል "STILL  WRITING The  Pleasures  and Perils  of  a Creative  Life" የሚል መፅሃፍ ለዓለሙ አበረከተች ሃሃሃሃ የስነፅሁፍ ወዳጆች በሙሉ ቢያነቡት ብዬ የምመኘው ስራ ነው። ስለ ስነፅሁፍ ብቻ ሳይሆን ስለ ህይወትም ጭምር ነው የምታወራው። ጥያቄው ጥልቀት ስላለው ይህ መፅሃፍ በጥልቀቱ ጥገት ልክ ለመመለስ የሞከረ ይመስለኛል። በዛውም የፅሁፍ ስራ እንደማንኛውም ስራ ያለውን ውጣ ውረድ ከራስ ተሞክሮ በተቀዳ እውነት በሚገባ ትዳስስበታለች። ያጣጥሙት ሃሃሃሃ


የሚገርመው የሚፅፉ ሰዎች ለምን እንደሚፅፉ ላያውቁም ይችላሉ። ማወቁ ግዳቸውም ላይሆን ይችላል። መልስ ፍለጋ የሚጠይቅ ሰው ግን መልሱን ለማግኘት ትንሽ መጣር አለበት ባይ ነኝ። መልስ የፈለገው እርሱ ነውና! ስለዚህ የአዳምን የስብሐት ጢም እና የዳኒ ሻፒሮን ስቲል ራይቲንግን አንብቦ የተወሰነ ስዕል ይኑረው ብዬ ነው። 


የዳኒ ፒዲኤፍ ይኸውላችሁ… Still writing


የአዳም እቴሜቴ ሎሚ ሽታን ግን ጋሽ ስብሐት እንደሚለው… ቢያሻችሁ ገዝታችሁ፣ ቢያሻችሁ ተውሳችሁ፣ ቢያሻችሁ ሰርቃችሁ አንብቡት… እንደ ፍጥርጥራችሁ ሃሃሃሃ 

iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement