Komentar baru

Advertisement

እኔና ፌስቡኬ…

Eriyot Alemu
Jun 27, 2017
Last Updated 2023-01-25T23:49:50Z
Advertisement


የግል ፌስቡኬ ከ1 see more በፊት…

★ ሃኒ የልጇን ፎቶ ገጭ አርጋዋለች… ወላድ በድባብ ትሂድ!

ከሃኒ ጋር የፌስቡክ ትውውቃችን ምንም ትዝ አይለኝም… እንዴት ጓደኛማቾች እንደሆንን ራሱ ዙከርበርግ ይወቀው… 

ስለዚህ የልጇ ፎቶ መሆኑን እንዴት አወኩ??? 

ፎቶውን ጠቅ አርጌ ወደ ኮመንቶቹ ተንደረደርኩ…
==> 22 ሰዎች "እንትፍ እንትፍ ያሳድግልሽ" ብለዋል
==> 2 ሰዎች "እልልልልል ያሳድግልን!" ብለዋል… አንዱ አጎቷ መሰለኝ፣ ጊዜ ወስጄ እስካጣራ ይቆየኝ… 
==> አንድ ኮማች የህፃኗን ስም ጠቅሳ (ፆታዋንም አሳውቃኝ)፣ ሃኒ ምጧ እንዴት እንደነበረ ዘግባ ገላገለችኝ… ላይክ አደረኩት እና ባክ አልኩኝ
⇧⇧⇧ ይሄ ድፍን ሶስት ደቂቃ ፈጀ።

★ ሙሼ ባለ ጥሩንባው ከች አለ…

ሙሼ ሞትን ቀለል አርጌ እንዳይ ካደረጉኝ ግለሰቦች መሃል አንዱ ነው… 365 ከነፋስ ቀን ይሄን "ታዋቂ፣ አዋቂ፣ ታታሪ…" እያለ የሚደረድረውን ሰው፣ ያለምንም ርዕራሄ ይፈጀዋል። በሙሼ ሁኔታ የቅርቤን ሰው ሞት  ቢያረዳኝ እንኳ የምደነግጥ አይመስለኝም… ለዚህም ይመስለኛል በሙሼ የሞት ዜናዎች ላይ ብቻ ከአርአይፒ ጋር ሎልም ያለው… 
ሙሼ:— "ታታሪው አየለ ባደረበት ቤት ወስጥ አረፈ"
ወይንሸት: — "የሞት ዜና እንደሆነ ገምቼ ነው… አየለ ግን የገሃዱ አልመስል አለኝ… ነፀብራቁ ነው እንዴ ሎል"
ሰላማዊት:— "@ወይን  ሎል አርአይፒ አዬ"
⇧⇧⇧ ይሄ ሁለት ደቂቃ ፈጀ። 


★ ቀጥሎ የሰዓሊው የተከስተ ምሳ ፊቴ ቀርቧል… 

ደነገጥኩኝ… አዲስ አመል ማምጣቱ ነው… በፍፁም ሁሌም ምግቧን ከምትፖስተው ማሪቱ ጋር ላነፃፅረው አልፈለኩም። ለዚ ነው አንዳች ጉድ ቢኖረው ነው ብዬ ፎቶውን ዙም ያረኩት።
የፆም በያይነት ነው… የቃሪያው ስንግ ተገምጧል። አብስትራክት አርጌ አስቤው፣ ተከስተ በቃሪያው መገመጥ ምን ሊለን ፈልጎ ነው ብዬ ሳወጣ ሳወርድ፣ ሰዓቴ መገመጡ ትውስ ሲለኝ ዘለልኩት።
በቃ ተከስተ የሚለው ነገር አቷል። ትኩረት መሳቡ ደሞ አዲስ አመል ሆኖበታል ማለት ነው… አለቀ በቃ ብዬ ግምገማዬን ስገመግም ሶስት ደቂቃ ተበልቻለሁ።

★ ጣሴ ገልባጩ መጣ…

ፕሮፋይል ፒክቸሩ ራሱ በእንጨት ላይ ተገልብጦ የተሰቀለ ጣሳ ነው። በጣሴ በኩል ሳልፍ አፌ ወስጥ ጉሽ ያለ ጉሽ ያለ ይሰማኛል። ጠጡም አትጠጡም፣ እጠጣለውም አይልም ሁሌ የመጠጥ ፎቶዎች ዳውንሎድ አርጎ ገፁ ላይ ይለጥፋል። የጣሴ ችግር አይገባኝም… በቃ ግን የተከስተን ምሳ አወራረድኩበት።
ይሄ እንኳ 45 ሰከንድ ነው የፈጀው።

★ የፈንዱሽ አስተያየት ከፖስቶች አሳረፈኝ…

አንድ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ላይ "ሃሃሃሃሃ የአሮጊቷ ነገር ይገርማል… የገዛ… " ብሎ ዶትዶት ዶት ይላል አስተያየቷ። የፈንዱሻን አመል አቀዋለሁ… ለሁሉም ሃሃሃ ማለቷን ባውቅም (የሙሼ የሞት ዜና ላይ ሁሉ አንዴ ሃሃሃሃ ብላ ሙሼ ተቆጥቷት አጥፍታዋለች)… ግን የአሮጊቷ ነገር ያለቺው ከንክኖኝ ረዥም ተጭኜ ዘለግ ያለው ፅሁፍ ጋር ደረስኩ። እውነትም የአሮጊቷ ነገር ያሳዝናል። ፈንዱሽ ግን ምን እንዳሳቃት አልገባኝም። በርግጥ ፖሳቹ የሚያስቅ ሰው ነው። ግን ይሄ ፖስት ፈፅሞ አያስቅም።

ፖስቱ 35 ግጨው፣ 45 ዕንባ በንባ እና 23 አፍ ከፍቶ መሳቅ ተለግሶታል። የፍቅረኛው ልብ ቅርፅ ሳይዘነጋ ማለት ነው።
ወይ አለም ሳቅ እና ለቅሶን እንደቀየጥሽ ዛሬም አለሽ… እያልኩ ስደመም ድፍን አራት ደቂቃዬን ተነጭቼ… ስባንን ሰው ሜዳ ላይ ነኝ። ቶሎ ክሊክ ክሊክ ወደ ሜዳዬ…

★ አጀቡሽ ከሰብስቤ ጋር ተሰበሰበች የሚል አስደሳች ዜና ላይ ደረስኩ። 

አላመነታሁም ኮመንት የሚለውን ተጫንኩትና "አጀቡሽዬ እንኳን ደስ አለሽ" ብዬ ከኮመትኩ በኋላ አንዳች ነገር ከነከነኝ። የሌሎቹን ኮመንት አንድ ባንድ አየሁ። ባብዛኛው ወይም በሌላ አገላለፅ በአመዛኙ "እንኳን ለዚህ አበቃቹ! እንኳን ደስ አላቹ!" ነው የሚሉት። ባዳነት ተሰምቶኝ ተሸማቀኩ። ወዲያው ኮመንቴን ኤዲት አደረኩት…
"አጀቡሽዬና እና ሰብስቤ እንኳን ተሰበሰባቹልን… መልካሙን ትዳር ያርግላቹ። ሆኖም ከላይ ሰብስቤ አፈሳት እንዲሁም ሰብስቤን አፈሰችው በሚሉት አስተያየት አልስማማም። የምን መተፋፈስ ነው… መጀመሪያ አስተያየት የሰጠው ሻሽ ነገር አናቱ ላይ ጣል ያረገው ልጅ እግር ቢጤ እንዳለው… መልካም ትዳር ይሁንላቹ" ብዬ ሁሉንም የማቃቸው አስመስዬ አስተያየቴን አሰፈርኩ። ሶስት ላይክ ተለገሰኝ… ሰብስቤም የጓደኛ እንሁን ጥያቄ ላከልኝ።
በድምሩ ኤዲትንግ ጨምሮ አምስጥ ደቂቃ እምጭጭ አረገ ይሄ ሂደት።

★ ሚሴጄ በራ እየበረርኩ ከፈትኩት…

ከላይ አስተያየት ላይ ያሰፈርኩት ባለ ሻሹ ሰውዬ ነው
"ስማ አንተ የት ታቀኝና ነው ባለሻሽ፣ ልጅ እግር የምትለው…" አለና የተመረጡ ስድቦች በትህትና ሰዳደበኝኝ። የገረመኝ የሰጠሁት አስተያየትን እኮ ላይክ መግጨቱ ነው። ከዛ ለመልስ ምት ብዬ ስለሱ ሳጣራ 20 ደቂቃ ተበላው። በንዴት "በአደባባይ አልጋ በሚሴጅ ቀጋ" ብዬ ብሎክ ደረገምኩት።

★ ኖቲፊኬሽን በራልኝ ደስ አለኝ… 

ኖቲፊኬሽን መጥፎም ጥሩም ነገር ያመጣል። እንዲሁ ቀድመው ሲያዩት ግን ደስ ይላል። ዋና ማጃጃያው እሱ ሳይሆን አይቀርም። ዶፓሚናም ብዬ ፈጥኜ ተጫንኩት። 
ትዝታው ነው… ከአራት አመት በፊት ፖስቼው የረሳሁት ፎቶ ላይ ኣስተያየት አስፍሯል።
"ይሄ ፎቶ በጣም ያምራል" ይላል አስተያየቱ… እቤታችን መቶ የእውነት አልበሜን ሰጥቼው እያየ ነው የሚመስለው። ሆኖም በስሱ እንኳ "አመሰግናለሁ" ብዬ እንዳልመልስ ያን ፎቶ ለፌስቡክ ጓደኞቼ ሁላ መቆስቆስ ሊሆንብኝ ነው። ዝም ብለውም ቅር ይለዋል። ስለዚህ አስተያየቱን ላይክ አድርጌ በምትኩ የሱ አልበም ውስጥ ሄጄ የልጅነት ፎቶውን ላይክ አርጌ ወጣሁ።

አንድ See more…
iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement