Komentar baru

Advertisement

ክልስ ፈጠራዎች!!!

Eriyot Alemu
Jan 4, 2017
Last Updated 2023-08-21T21:21:51Z
Advertisement




አለ እንዴ!?
ካልነበር አለም ዉስጥ ያልነበር አፍልቆ
የታየ በምድር ከሰው ልጆች ልቆ?
አረ የለም!
ህይወት ለሰው ልጅ ዘር እንዲማ አደለም:: 

ዛሬ ባይኑ የገባ፣ በጆሮው የላከው
ነገ ነበር ሆኖ፣ ንብረት እየሆነው 
ነበር እያጋጨ ያልነበር ያፈልቃል
በነበሩ መጠን
የፈጠራው ወሰን
ይሰፋል፤ ይጠባል::

አለ እንዴ!?
ድንጋዮች ሳያጋጭ ከምንም ነገር ላይ
እሳት ያፈለቀ?
ወፍ ሚባል ሳያይ
ስላየር ላይ መስፈፍ በራሱ ያወቀ?

ያስብ ነበር እንዴ!?
አንድ ወጥ የሆነ አለት፣ ድንጋዩን ፍልፈላ
ግንደ ቆርቁር ባያይ ቅዱስ ላሊበላ
የሚያሰፋው ሳይኖር የምናቡን ኬላ
ይመጣለት ነበር በዝምብሎ መላ?
እንጃ!

አረ ደሞ ማነው?
አብዮት ጀማሪ፣ ነጻነት አምጣቂ
አርነት መውጣትን ምድር ላይ ፈንጣቂ
ከወንድም አህዮች ባሳብ ተገንጥሎ
የነጻነት ማተብ በልቡ አንጠልጥሎ
ጎዳና የወጣ ሜዳ ላይ ሰፋሪ
ከሜዳ አ'ያ ቀድሞ ማን ነበር ያለ እሪ?

ደግሞስ!
የጥንት የሰው ልጆች ገና ሳሉ ፋራ
ገዥዎች ነን ብለው፣ ሳይለዩ ሳል ጎራ
ከዛፍ ዛፍ በመዝለል እየቆሉ ጭራ
ባንድነት ሲኖሩ ከፍጥረቱ ጋራ
ድንገት ቢያዩም አይደል የወፎቹን ጎጆ
ንድፉን ዱቅ ያረገው ጭንቅላት ኮርጆ?
መሰለኝ!

ታድያ!
በኛ ግድ አልባነት
የኛን ብቻ ስንኖር በስግብግብነት
ጥቅሙ ያልታወቀን ከተፈጥሮ አንዱ
መንምኖ መንምኖ ሲጠፋ ዘር ግንዱ
 ....... እንላለን እንዴ?
አንድ ቋንቋ ጠፋ አንድ እውቀት ጎደለ
ባናውቅም ከኗሪው ምን እንደገደለ?

ብቻ!
ተፈጥሮና እኛ ቋንቋችን ባቢሎን
ነው ብለን ስንኖር፣ ያልተግባባን መስሎን
ቅድመ ሙሌት ሆነው የሚያወሩት ቋንቋ
መነሻዎች ናቸው ከሰው ዘር ለነቃ!!!
iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement