Komentar baru

Advertisement

አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን ማጥፋት ማለት!!!

Eriyot Alemu
Dec 21, 2016
Last Updated 2023-01-04T19:29:45Z
Advertisement
ትላንት ማታ!
"አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን አጠፋለው
በቃ ተስፋ ቁረጭ ያኔ እረሳሻለው።"
ብዬ ቻዎ ብዬሽ፣ ካልጋ ላይ ከርሜ
ጠዋት አንቺን ተክቶ፣ "እሪ" ሲል አላርሜ
እየተነጫነጭኩ ነቅቼ ከእንቅልፌ
አንቺን ማሰብ ጀመርኩ ትራሴን ታቅፌ 
እሷ ብትኖር ኖሮ… 
እሷ ብትኖር ኖሮ ደንግጬ አልነሳም
ጨፍኜ እነቃለው ልክ ጉንጬ ሲሳም
እያልኩኝ በድንገት አንቺን በማሰቤ
አላርሜን ሰበርኩት እሱ ነው ሰበቤ
"አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን አጠፋለው
በቃ ተስፋ ቁረጭ ያኔ እረሳሻለው።"
አልኩኝ ተመልሼ
ራሴን ቀልሼ

ካልጋ ላይ ወርጄ ቀስቀስ ስል ገና
ፆሜን ሊያስታውሰኝ የውስጤ በገና
መደርደር ሲጀምር በባዶ ሆዴ ላይ
መኖሬ ትዝ ብሎኝ ይሄን ሁሉ ሳላይ
ድንገት አስታወስኩሽ እሷ ብትኖር ብዬ
ቁርስጋ እደርስ ነበር ሆድ አቀባብዬ
እያልኩኝ ሳላውቀው አንቺን በማሰቤ
ቁርሴንም ሰረዝኩት እሱ ነው ሰበቤ።
"አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን አጠፋለው
በቃ ተስፋ ቁረጭ ያኔ እረሳሻለው።"
አልኩኝ ተመልሼ
ራሴን ቀልሼ


በሬን ዘጋሁና ከቤቴ ወጥቼ
ጉዞ እንደጀመርኩኝ አንቺን ጎኔ አጥቼ
መንገዱም ራሱ ቀድሞ እንደማያቀኝ
ቁና ቁና አስብሎ በብዙ አስጨነቀኝ።
ካንቺ ጋር ስራመድ,,,,
ካንቺ ጋር ስራመድ አጭር የነበረው
ያለቅጥ ረዝሞ ወይኔ መንገድ ቀረው
እያልኩኝ አሁንም አንቺን በማሰቤ
መንገዴን ቀየርኩት እሱ ነው ሰበቤ
"አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን አጠፋለው"
ምን ማለት ነው ታድያ? አሁን ጠይቄያለው።


አንቺን የሚያስታውስ ሁሉን ማጥፋት ማለት
ማለቂያ የሌለው ረዥም ሰንሰለት
ነውና የሚያጠፋ እኔኑ ጨምሮ፣
አንደቤቴ ላይስት ከትላንት ተምሮ
ይኸው ፊትሽ ቆሟል! የፊጥኝ ታስሮ፣
ያንቺ አንደበት ይፍታው ይቅርታን አብስሮ።
ይቅር በይኝ በቃ!!!!!!
iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement