Advertisement
*** መጀመሪያ ቀን
አንድ ሁለት ሶስት አራት እስኪ ቁጥር ጥሩ,,,, ቁጥርጥሩ,,, ጥሩ ተጀመረ።
ከኛ ቤት በላይ ዳገት አለ። ዳገቱ ላይ ቤቶች አሉ። ቤቶቹ ውስጥ ሰዎች አሉ። ውሻም ያላቸው አሉ። አይጦችም ያላቸው አሉ። የሳሎን አይጥ ግን አለ?

*
ያመዋል ይላሉ። አንድም ቀን ሆዴን አሞኝ አያቅም። አሞኛል አሞኛል አሞኛል በጠና,,,, እባካችሁ ሰዎች ውሰዱኝ ቀበና,,, ቀበና በአውቶብስ ሩቅ ነው። በታክሲ ግን ቅርብ መሰለኝ።
*
ከእንቅልፌ ተነስቼ ፊቴን ስታጠብ ጆጉ ውስጥ ድንች አገኘው። ወንዝ ዳር የበቀለ ድንች ይመስላል። እንዴት በቧንቧው አለፈ ታድያ?
*** ሌላ ቀን
ከቤቴ እንደ ወጣው እትየ ሸዋሮቢት አገኙኝ። እኔ ነኝ ያወጣሁላቸው። ሁሌ ከዘራ ስለሚይዙ ሮቦት ይመስሉኛል። ከዛ ሴት ስለሆኑ ሮቢት አልኳቸው,,, ሸዋሮቢት። ሳያቸው ስለሚያስቁኝ እስቃለው። ፍልቅልቁ ይሉኛል። ፈለቀ ማለታቸው ነው ብዬ አቤት እላቸዋለው። ስድስተኛ ክፍል አብሮኝ የተማረ ልጅ ነው ፈለቀ።
*
በስማም ዳገቱ አናት ላይ ሱቁ ጋር ያለው ሰውዬ አሁንም እያጨሰ አየሁት። ባለፈው "ለኩላሊትህ ጥሩ አይደለም። እንኳን ያንተ የዶሮ ኩላሊት ተጠብሶ ይበላል" ብዬው ነበር። እሱም ምን እንዳሳቀው ባይገባኝም። እንካ ተጠብሶ ለማይበላው ድድህ ጥሩ ነው አለኝ። ድዳም።
*** ሌላ ሌላ ቀን
ፈረስ በጣም እወዳለው። የምጋልበው ግን አህያ ነው። አቤት ዶሮ ስታስጠላኝ። አንዴ እንቁላል ልትጥል ስትል ተከትዬ ሳያት እንቁላሏን ጥላብኝ ሄደች። ሳትኳት እንጂ በእንቁላሏ ልፈነክታት ነበር።
*
የእረፍት ጊዜዬን በመተኛትና መፅሃፍ ላይ በመተኛት ነው የማሳልፈው። ሰዎችም መፅሃፍ ይሰጡኛል። ስጦታ እያሉ። ገንዘብ አይሰጡኝም ነበር። መፅሃፍ እገዛበት ነበር።
*
እንቅልፌ ሲመጣ ካልጋዬ ወርጄ ስፖርት እሰራለው። ከዛም ተመልሼ እተኛና አስባለው። እመራመራለው።ሁለት ሸረሪቶች አሉኝ። እግራቸውን ስቆርጠው ስቆርጠው አላልቅ ሲለኝ ዶሮ በሆነች አልኩኝ። ለካ ሰውም ሁለት ጆሮ ነው ያለው።
*
ቴሌቪዥን አላይም በጣም ነው የምጠላው። ድራማ እና ፊልም ግን ነፍሴ ነው። ሌላ የማልወደው አጎቴን ነው። ሲያወራ ምግብ የሚበላ ነው የሚመስለኝ። ደሞ ሲተኛ አያንኮራፉም። ቢያንኮራፉማ ለእንቅልፌ ይጠቅመኝ ነበር።
*** ሌላማ ቀን
ጠዋት ተነስቼ ተከዝኩ። ቀኑ ብሩህ ነው። አይለኛ ዝናብ ዘንቦ ነበር። የአውሮፕላን ድምፅ ሰማው። ለምን ግን አውሮፕላን እንደ ወፎች እግር መቆንጠጫ የለውም? አጎቴ መላጣ ነው። አንዴ መላጣው ላይ ዝንብ ስታርፍ በስፒል የወጋችው ነው የሚመስለው። እንዴት ደስ እንዳለኝ። ግን አውሮፕላን መቆንጠጫ ቢኖረው አስፓልቱ ያሳዝነኝ ነበር።
*
አንዳንድ ለማኞች ይገርሙኛል። እሁድ እንኳን አያርፉም። ስራ ይወዳሉ በጣም። ግብር አይከፍሉም ይላል አጎቴ። እሰይ አበጁ። ላባቸውን ጠብ አርገው ለምንድነው የሚከፍሉት።
*
አጎቴ መጣ። የሚደክመኝ አይመስለውም። ምናለ ሶስቴ ቢያንኳኳ። አምስቴ ከሚያንኳኳ።
*** ጠዋት
ዛሬ ጨረቃ ሙሉ ሆነች። ከዛ ጣሪያ ለይ ወጥቼ ማሰብ ጀመርኩ። ጨረቃ አንዳንዴ ብርቱካን አንዳንዴ ሙዝ ትመስላለች። ፍራፍሬ ሳትወድ አትቀርም። ፀሃይ ግን ሁሌ ኳስ ትመስላለች። እኔ ደሞ በቀን ኳስ ማየት አልወድም።
*
አንድ ዘመዳችን ካገር ቤት መጣ። ካልጋ ላይ ሊያስወርደኝ ነው ብዬ ስበሳጭ የሳይንስ ተማሪ ነኝ ሲለኝ ተረጋጋው። ካገር ቤት ስለመጣ የቆሎ ተማሪ መስሎኝ ነበር። የሚገርመኝ ግን የቆሎ ተማሪዎች ሁሌ ስለ ቆሎ መማር ምን ይሰራላቸዋል? ለምንድን ነው አንዳንዴ ስለ ሳይንስ የማይማሩት?
*** ታህሳስ ሶስት ክረምት
እኛ ሰፈር አንዲት ጥሩ ልጅ አለች። ባለፈው ጥርስህን ተበጥረኸው ነው ወይ አለችኝ። በጣም ወደድኳት። አጎቴ ሁሌ ለምንድነው ፀጉርህን የማታበጥረው እያለ ይጨቀጭኝ ነበር። ከዛ በጣም ስለምወዳት ቤታቸው ሄጄ አፍንጫሽ አትክልት ውሃ ማጠጫ ዕቃ ይመስላል አልኳት። ግን አልገባትም። እንደ ናይጄሪያዎች ወደላይ የተገለበጠ ነው… ባፍሽ ውሃ ስጠጪ ባፍንጫ የሚወጣ ይመስላል ብዬ ሳስረዳት በጥፊ መታችኝ። በጣም ፈነጠዝኩ… አጎቴ ከጓደኛው ጋር ሲያወሩ ልጅ ሆኖ ብዙ ጊዜ መመታቱን ሲያወራ ስሰማ እቀና ነበር። በርግጫ ብትመታኝ ግን እንዴት ልሆን ነው። በጣም ጥሩ ሰው ነች።
*
በራድዮ ቡናን ያገኘችው ፍየል እንደሆነች ሲነገር ሰማው። ከዛ በኋላ የጎረቤታችንን ፍየል በጣም ተከታተልኩት። አንድ ቀን ኮባ ሲበላ አየሁት። ከዛ ይጨፍራል ብዬ ስጠብቅ ስጠብቅ አልጨፈረም። የነ ካሊድ ፍየል ቢሆን ግን ይጨፍር ነበር። እሱ ጭፈራ ይወዳል። ስላልጨፈረ ብዬ አልተውኩትም ኮባውን ቆርጬ በላሁት። እኔም ግን አልጨፈርኩም። ወይ ኮባ ተጠብሶ ነው የሚበላው መሰለኝ።
*** የደስታዬ ቀን
ዛሬ አጎቴ ሃኪም ቤት ወሰደኝ። ከዛ ሃኪሙ አፍህን ክፈት አለኝ። አፌ ወስጥ ምን እንደሚፈልግ እኔንጃ… ባትሪ ይዟል። ፈለገ ፈለገና ምላስህንም አውጣ አለኝ። ዞር ስል ካጠገቤ መቀስ አየው። ምላሴን ሊቆርጠው ከሆነ ብዬ በደንብ አወጣሁበት። ምላሴ ግን ረዥም አይደለም። ያጎቴ እጮኛ ግን ምላሷ ረዥም ነው። አጎቴ ሲል እንጂ አይቼው አላቅም። ሃኪሙም በቃ አፍህን ዝጋ ብሎኝ ካጎቴ ጋር ተነጋገሩና ወደቤት ሄድን።
*
አሞሃል ተኛ ተብዬ ተኛው። እትየ ሸዋሮቢት ከኢትፍሩት የገዙትን ብርቱካን እየላጡ ካጎቴ ጋር መብላት ጀመሩ። እኔ ብስኩት ቢያመጡ ነበር የሚሻለኝ። ግን ትልቅ ሰው ብስኩት የሚበላው ተደብቆ ነው። በሽታ ተከላካይ መሃድን ቢበላ ጥሩ ነው ሲሉ ሰማዋቸው። በስማም አስጠሉኝ,,, ለካ ሚስማር ስለሚበሉ ነው የማያማቸው። ለነገሩ በቴሌቪዥን አምፖልም የሚበሉ ሰዎች አይቻለው።
*** በዛ በበጋ
ዝናብ ሲዘንብ እየሮጥኩ ሄጄ ተኛው። ጣሪያው ግን ረበሸኝ። ለዚ ለዚ ሲባል ጣሪያው ክፍት መሆን ነበረበት። ጆሮዬን ያዝ ለቀቅ እያረኩ ዝንቡን ሳዳምጠው በጣም ደስ ይላል። ከዛ አጎቴም ደስ ይበለው ብዬ በተኛበት ሄጄ ጆሮውን ያዝ ለቀቅ ሳረገው,,,, ተነሳና እየደበደበ ከቤት አስወጣኝ።
*
አጎቴ ጓደኛውን ብዙ ጊዜ ጭራህን ትቆላለህ ሲለው ስለምሰማ እንሽላሊት ይመስለኛል። እኛ ቤት አያድርም እንጂ በተኛበት ጭራውን ቆርጬ እበላው ነበር። ከዛ እንደነ ከማል ውሻ ሰው ሁሉ ይፈራኝ ነበር።